የአባለዘር በሽታዎች በግብረስጋ ግንኙነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ ህመሞች ናቸው፤ እነዚህ በሽታዎች ብዙውን ጊዜ ወጣቱን የማህበረሰብ አካል በማጥቃት ይታወቃሉ፤ ነገር ግን ጥንቃቄ የሌለው ግብረስጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሁሉም ሰው ለህመሙ የመጋለጥ እድሉ ተመሳሳይ ነው። የአባለዘር በሽታዎች ከአድሎ እና መገለል ፍራቻ ጋር በተያያዘ ታማሚዎች የህክምና እርዳታን ባለመጠየቃቸው በቀላሉ መታከም ቢችሉም እንኳን አላስፈላጊ ውጤቶች አስከትለው ሊመጡ ይችላሉ፤ በተለይም መሃንነት አብዛኛውን ጊዜ የሚከተለው እና አሳዛኝ የሆነ አስከፊ ጉዳቱ ነው ፤ ከማህጸን ውጭ የሆነ እርግዝና፣ ቁስለት እና የስነልቦና ጉዳትም የሚጠበቁ አስከፊ ጉዳቶች ናቸው በመሆኑም ምልክቶቹን ሲመለከቱ እራስን እና የትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛን በማስመርመር እና ተገቢውን ህክምና በማግኘት እነዚህን ጉዳቶች በቀላሉ መከላከል ይቻላል።
ብዙ አይነት ባክቴሪያ እና ቫይረሶች የአባለዘር በሽታዎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ በመሆኑም የተለያዩ አይነት ምልክቶች ያሳያሉ ቀጣይ የተዘረዘሩት የተለመዱ ምልክቶች ናቸው - ሲሸኑ ማቃጠል -ከብልት የሚወጣ ያልተለመደ ፈሳሽ -የብልት መቁሰ ል -ከእንብርት በታች ያለ የሆድ ህመም
የመ ህጎችን መጠቀም
- መታቀብ (ከግብረ ስጋ ግንኙነት መቆጠብ)
- መወሰን (ግብረስጋ ግንኙነትን ከአንድ ሰው ጋር ብቻ መፈጸም)
- መጠንቀቅ(ኮንዶም መጠቀም)
የአባላዘር በሽታዎች የህመሞቹን ምልክት በመለየት የሚታከሙ በሽታዎች ሲሆኑ ነገር ግን የኤች ኣይ ቪ ምርመራ አብሮ ቢደረግ ይመከራል።
እንደመንስኤው የተለያዩ የህክምና አማራጮች ያሉ ሲሆን ከሚሰጡት መድሃኒቶች መካከል የተወሰኑት፡
- Ceftriaxone
- Azithromycin
- Metronidazole
- Acyclovir
- Penicillin G
- መካን መሆን
- ከማህጸን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና
- የኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ የሰውነት አካላት መንሰራፋት
- የስነ-ልቦና ጫና
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.