ዳማከሴDamakese

የአባለዘር በሽታዎች

የአባለዘር በሽታዎች በግብረስጋ ግንኙነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ ህመሞች ናቸው፤  እነዚህ በሽታዎች ብዙውን ጊዜ ወጣቱን የማህበረሰብ አካል በማጥቃት ይታወቃሉ፤ ነገር ግን ጥንቃቄ የሌለው ግብረስጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሁሉም ሰው ለህመሙ የመጋለጥ እድሉ ተመሳሳይ ነው። የአባለዘር በሽታዎች ከአድሎ እና መገለል ፍራቻ ጋር በተያያዘ ታማሚዎች የህክምና እርዳታን ባለመጠየቃቸው በቀላሉ መታከም ቢችሉም እንኳን አላስፈላጊ ውጤቶች አስከትለው ሊመጡ ይችላሉ፤ በተለይም መሃንነት አብዛኛውን ጊዜ የሚከተለው እና አሳዛኝ የሆነ አስከፊ ጉዳቱ ነው ፤ ከማህጸን ውጭ የሆነ እርግዝና፣ ቁስለት እና የስነልቦና ጉዳትም የሚጠበቁ አስከፊ ጉዳቶች ናቸው በመሆኑም ምልክቶቹን ሲመለከቱ እራስን እና የትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛን በማስመርመር እና ተገቢውን ህክምና በማግኘት እነዚህን ጉዳቶች በቀላሉ መከላከል ይቻላል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።