የማህጸን ጫፍ ካንሰር የተበላሹ ህዋሶች ቁጥጥር በሌለው ሁኔታ ማደግ የሚከሰት ህመም ነው። በሴቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች አንዱ ነው። በአማካኝ ከ50 ዓመት እድሜ ላይ የሚገኝ በሽታ ሲሆን በቅርብ አመታት ውስጥ ካንሰሩ ላይ ያለውን የግንዛቤ መጠን በመጨመር እና ቅድመ ምርመራ በማድረግ በካንሰሩ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ረድቷል። ለህመሙ መከሰት ዋነኛ መንሰኤው HPV በሚባለው ቫይረስ መያዝ ነው።
- ከ16 ዓመት እድሜ በፊት የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ መጀመር
- ብዙ የፍቅር አጋሮች መኖር
- ኮንዶም ያለመጠቀም
- የኤች አይ ቪ ህመም ተጠቂ መሆን
- ትንባሆ ማጨስ
- መጥፎ ሽታ ሊኖረው የሚችል ደም የተቀላቀለው ፈሳሽ ከማህጸን መፍሰስ
- ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ, በወር አበባ ጊዜያት መካከል ወይም ከማረጥ በኋላ የሚከሰት ክማህጸን የሚፈስ ደም።
- ድካም
- የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ ካንሰሩ አቅራቢያ ወደሚገኙ የሰውነት አካላት ሲንሰራፋ የሚኖሩ ምልክቶች፡
- ሽንት መሽናት ላይ መቸገር (መቋጠር)
- ከሽንት ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣ ደም
- ተቅማጥ
- የፊንጢጣዎ ህመም ወይም ደም መፍሰስ
- የጀርባ ህመም
- የእግር መደንዘዝ እና አልታዘዝም ማለት
- የHPV ክትባት መከተብ- ይህ ከ9 ዓመት እድሜ ጀምሮ መሰጠት የሚቻል ክትባት ሲሆን ከ26 ዓመት በኋላ ግን መሰጠት አይመከርም
- ኮንዶም መጠቀም
- ተጓዳኝ በሽታዎች ሲኖሩ በትክክል መከታተል እና የበሽታ መከላከል አቅምን መጨመር
- ትንባሆ አለማጨስ
- የማህጸን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ ናቸው
- ይህም ከ21-29 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ በየ3 ዓመት ልዩነት የሚደረግ ፓፕ ስሚር ምርመራ
- ከ30-65 እድሜ ክልል ላሉ ሴቶች ደግሞ በየ3 ዓመት ልዩነት የሚደረግ ፓፕ ስሚር ምርመራ እደቀጠለ ሆኖ ተጨማሪ በየ5 አመት ልዩነት የሚደረገ የHPV እና ፓፕ ስሚር ምርመራ ነው።
- ፓፕ ስሚር
- አሴቲክ አሲድን በመጠቀም የሚደረግ ምርመራ
- የማህጸን ጫፍ ላይ የሚታይ አጠራጣሪ ነገር ካለ ናሙና ወስዶ መመርመር
- የማህጸን ጫፍ ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ መሰራፋቱን ለማጣራት የሚደረጉ የደም ምርመራ፣ ራጅ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ምርመራዎች አሉ።
- የቀዶ ህክምና
- ኬሞ ቴራፒ
- የጨረር ህክምና ናቸው።
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.