ዳማከሴDamakese

የማህጸን ጫፍ ካንሰር

የማህጸን ጫፍ ካንሰር የተበላሹ ህዋሶች ቁጥጥር በሌለው ሁኔታ ማደግ የሚከሰት ህመም ነው። በሴቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች አንዱ ነው። በአማካኝ ከ50 ዓመት እድሜ ላይ የሚገኝ በሽታ ሲሆን በቅርብ አመታት ውስጥ ካንሰሩ ላይ ያለውን የግንዛቤ መጠን በመጨመር እና ቅድመ ምርመራ በማድረግ በካንሰሩ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ረድቷል። ለህመሙ መከሰት ዋነኛ መንሰኤው HPV በሚባለው ቫይረስ መያዝ ነው።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።