ብጉንጅ ከፍተኛ ህመም የሚያመጣ እና መግል በቆዳ ውስጥ ሲጠራቀም የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው። ቀላ ያለ እብጠት በመፍጠር ይታወቃል። ይህ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት ህመም ሲሆን፤ በቆዳ ላይ በተፈጥሮ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ወደ ውስጠኛው የቆዳ ክፍል ሲገቡ የሚፈጠር ህመም ነው። እብጠቱ በመጠን እና በህመም እየጨመረ እስከሚፈነዳ ድረስ ይቀጥላል። ታካሚዎች እብጠቱን ለማፈንዳት መሞከር የለባቸውም ይህም ኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ የቆዳ ክፍል እንዲንሰራፋ ስለሚያረግ ነው። ብዙ ብጉንጆች አንድ ቦታ ሰብሰብ ብለው ተለቅ ያለ እብጠት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይህ ካርበንክል የምንለው ነው።
- ቀይ እብጠት
- በቀናት ልዩነት እብጠቱ እየጨመረ ይሄዳል
- የእብጠቱ ጫፍ ላይ የሚኖር ነጭ ቀለም
- የበሽታ መከላከል አቅም ዝቅ ማለት
- የስኳር በሽታ
- በብጉንጅ ከታመመ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ መኖር
- ሌሎች የቆዳ ህመሞች ሲኖሩ
የሚቀቡ እና የሚዋጡ አንቲባዮቲክስ እንደ በሽታው ክብደት በሃኪሞ ይታዘዛል እነዚህም ፡
- Mupirocin cream
- Cloxacillin(የሚዋጥ)
- Cephalexin(የሚዋጥ)
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.