ዳማከሴDamakese

ብጉንጅ

ብጉንጅ ከፍተኛ ህመም የሚያመጣ እና መግል በቆዳ ውስጥ ሲጠራቀም የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው። ቀላ ያለ እብጠት በመፍጠር ይታወቃል። ይህ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት ህመም ሲሆን፤ በቆዳ ላይ በተፈጥሮ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ወደ ውስጠኛው የቆዳ ክፍል ሲገቡ የሚፈጠር ህመም ነው። እብጠቱ በመጠን እና በህመም እየጨመረ እስከሚፈነዳ ድረስ ይቀጥላል። ታካሚዎች እብጠቱን ለማፈንዳት መሞከር የለባቸውም ይህም ኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ የቆዳ ክፍል እንዲንሰራፋ ስለሚያረግ ነው። ብዙ ብጉንጆች አንድ ቦታ ሰብሰብ ብለው ተለቅ ያለ እብጠት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይህ ካርበንክል የምንለው ነው።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።