ከኩላሊት ተነስቶ ሽንትን ወደ የሽንት ፊኛ የሚወስደው ቧንቧ፣ የሽንት ፊኛ እና ሽንትን ወደ ውጭ
የምናስወግድበት የመጨረሻው ቧንቧ በባክቴሪያ ሲጠቁ የሚፈጠር ህመም ነው።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ለሁለት ይከፈላላ እነዚህም
- ከፊኛ በላይ የሚኖር እና ጸና ያለው ኢንፈክሽን እና
- የሽንት ፊኛን እና የታችኛውን የሽንት ቧንባ የሚያጠቃ ኢንፈክሽን ናቸው። አስር እጥፍ ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን ይህ የሆነው የመጨረሻው ቧንቧ በሴቶች ላይ በጣም አጭር ስለሆነ እና ባክቴሪያዎች በቀላሉ ወደ ላይ የመውጣት እድል ስላላቸው ነው። የወንዶች ብልት ግን በቍመት በአማካኝ 20 ሴሜ ያህል ስለሆነ ባክቴሪያዎች በቀላሉ የሽንት ቧንቧውን የማጥቃት እድል ስለሌላቸው ነው። በመሆኑም ይህ በሽታ በተለይ ከ 1-50 ዓመት ላይ የሆነ ወንድ ላይ ሲፈጠር በሽንት ቧንቧው አፈጣጠር ላይ ችግር ሊኖር ስለሚችል የበለጠ የማጣሪያ ምርመራ መደረግ ይገባል።
- ጥንቃቂ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ማረግ
- የሚያጣብቅ የውስጥ ሱሪ ማድረግ
- ከኋላ ወደ ፊት ብልትን መጥረግ
- በሽንት ቧንቧ አፈጣጠር ላይ ያለ እና የሽንትን መንገድ የሚያስተጓጉል ችግር
- የስኳር በሽታ
- በቂ ውሃ ያለመጠጣት ይገኙበታል።
- የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት እንዲሁም ማጣደፍ
- ሲሸኑ ማቃጠል
- ከእንብርት በታች የሚሰማ ህመም
- የሽንት ቀለም እና ጠረን መቀየር (የታችኛው ኢንፌክሽን ላይ የሚታዩ ምልክቶች ሲሆኑ)
- ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት
- ሽንጥ ላይ የሚሰማ የሚደነዝዝ አይነት ህመም (የላይኛው ኢንፌክሽን ላይ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው)
- በቂ ውሃ መጠጣት
- ጥንቃቄ የተሞላበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
- ንጽህናን መጠበቅ እና የመሳስሉትን መተግበር ያስፈልጋል በተጨማሪም አንዳንድ ሴቶች ከግብረ ስጋ ግንኙነት ጋር የተቆራኘ በተደጋጋሚ የሚከሰት ኢንፌክሽን ሊያጋጥማቸው ይችላል ይህ ሲፈጠር ሁለት አማራጮችን መጠቀም ይቻላል፡
- ግብረ ስጋ ግንኙኘት ሲያደርጉ የሚወሰድ መድሃኒት መጠቀም
- ምልክቶቹን በመማር ኢንፈክሽኑ ሲፈጠር መድሃኒቱን በራሳቸው መውሰድ ናቸው።
የታማሚ ምልክት አብዛኛውን ጊዜ ህመሙ ላይ ለመድረስ እና ተገቢውን መድሃኒት ለመስጠት በቂ ነው። የሽንት ምርመራ፣ የደም ምርመራ፣ አልትራሳውንድ(የላይኛው የሽንት ቧንቧ ሲጠቃ ሚደረግ ምርመራ ነው) ተጨማሪ ምርመራዎች እንደ አስፈላጊነቱ በሃኪሞ ሊታዘዝ ይችላል።
የሚዋጡ የኢንፈክሽን መድሃኒቶች ብዙውን ጊዜ በቂ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ፡ Ciprofloxacin, Nitrofurantoin, Cotrimoxazole ይገኙበታል። ህመሙ ሲጸና(ከፍተኛ ትኩሳት፣ የልብ ምት መጨመር፣ የታማሚው ንቃት መጠን መቀነስ) ሲኖሩ አስተኝቶ በደም ስር በሚሰጡ መድሃኒቶች ማከም ያስፈልጋል። በሽታው የተለመደ እና በተደጋጋሚ የሚፈጠር ቢሆንም እንኳን መዘናጋት ተገቢ አይደለም ምክንያቱም በተደጋጋሚ የሚፈጠር ኢንፌክሽን የኩላሊት እና የሽንት ቧንቧ ላይ ጠባሳ በማምጣት እስከ ኩላሊት መድከም የሚደርስ አስከፊ ውጤት ሊያደርስ ይችላል።
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.