ዳማከሴDamakese

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

ከኩላሊት ተነስቶ ሽንትን ወደ የሽንት ፊኛ የሚወስደው ቧንቧ፣ የሽንት ፊኛ እና ሽንትን ወደ ውጭ የምናስወግድበት የመጨረሻው ቧንቧ በባክቴሪያ ሲጠቁ የሚፈጠር ህመም ነው።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ለሁለት ይከፈላላ እነዚህም

  • ከፊኛ በላይ የሚኖር እና ጸና ያለው ኢንፈክሽን እና
  • የሽንት ፊኛን እና የታችኛውን የሽንት ቧንባ የሚያጠቃ ኢንፈክሽን ናቸው። አስር እጥፍ ሴቶችን የሚያጠቃ ሲሆን ይህ የሆነው የመጨረሻው ቧንቧ በሴቶች ላይ በጣም አጭር ስለሆነ እና ባክቴሪያዎች በቀላሉ ወደ ላይ የመውጣት እድል ስላላቸው ነው። የወንዶች ብልት ግን በቍመት በአማካኝ 20 ሴሜ ያህል ስለሆነ ባክቴሪያዎች በቀላሉ የሽንት ቧንቧውን የማጥቃት እድል ስለሌላቸው ነው። በመሆኑም ይህ በሽታ በተለይ ከ 1-50 ዓመት ላይ የሆነ ወንድ ላይ ሲፈጠር በሽንት ቧንቧው አፈጣጠር ላይ ችግር ሊኖር ስለሚችል የበለጠ የማጣሪያ ምርመራ መደረግ ይገባል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።