የባይፖላር ህመም ሥር የሰደደ የስሜት መረበሽ ሲሆን በስሜት፣ በአስተሳሰብ፣ በንቃት እና በባህርይ ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ያደርጋል። ማኒክ እና ሃይፖማኒክ መሆን የበሽታው ዋና ምልክት ናቸው። ባይፖላር ለማከም ከበድ የሚል እና በታካሚው፣ በቤተሰቡ እና በሃገር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና የሚያደርስ ህመም ነው። አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ በባፖላር የመጠቃት 0.5-1% እድል አለው። ሴቶች እና ወንዶች እኩል የመታመም እድል አላቸው። ባይፖላር I እና ባይፖላር II ተብሎ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን፣
- ባይፖላር I የማኒያ ምልክት ከድባቴ ጋር አንድላይ አርጎ የሚይዝ ሲሆን
- ባይፖላር II ደግሞ የሃይፖማኒያ ምልክትን ከድባቴ ጋር አንድላይ አርጎ የሚያሳይ ህመም ነው።
- የአንጎል ንጥረነገሮች መዛባት
- በዘር ውስጥ የታመመ ሰው መኖር
- የአስተዳደግ እና ማህበራዊ ችግር
ማኒያ
- ከታች የተገለጹትን ምልክቶች ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ማስተናገድ ማኒያ ያስብለዋል
- ከመጠን በላይ የሆነ ደስታ እና ተስፋ
- ድንገተኛ እና ከባድ የስሜት ለውጦች፣ ለምሳሌ ከደስታ ወደ ቁጣ ቶሎ መለዋወጥ
- እረፍት ማጣት ፣ መንቀዥቀዥ
- ፈጣን ንግግር ፣ የሃሳብ መሯሯጥ
- የኃይል መጨመር እና የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ
- የስሜታዊነት መጨመር እና ደካማ የማመዛዘን ችሎታ ለምሳሌ በድንገት ስራዎን ማቆም ትልቅ እና የማይጨረስ እቅድ ማውጣት።
- እንደ አደንዛዥ እፅ እና አልኮል አላግባብ መጠቀም እና ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነትን የመሳሰሉ ጥንቃቄ የጎደለው እና ለአደጋ የሚያጋልጥ ባህሪ ማሳየት
- ልተለመደ ሁኔታ አስፈላጊ፣ ጎበዝ ወይም ሀይለኛ እንደሆኑ መሰማት
- ባህሪያቸው የሚያደርሰውን አሉታዊ ተጽኖ ያለማወቅ ሃይፖማኒያ
- የማኒያ ምልክቶች በቀነሰ መጠን ሲታዩ እና ከ 4 ቀን እስከ 1 ሳምንት የሚቆዩ ከሆነ ሃይፖማኒአ ይባላሉ። ድባቴ
- የድባቴ ምልክቶች ከማኒያ ወይም ከሃይፖማኒያ ጋር በመቀያየር ይታያሉ እነዚህም ከፍተኛ የሀዘን ስሜት ፣ዝቅተኛ ጉልበት እና ተነሳሽነት ማጣት፣ ድካም፣ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወይም ዋጋ ቢስነት በአንድ ወቅት ለእርስዎ አስደሳች በሆኑ ነገሮች ደስታ ማጣት ፣የማተኮር እና ውሳኔዎችን የማድረግ ችግር፣ ያለምክንያት ማልቀስ
- የመድሃኒት ህክምና Lithium, valproate, lamotrigine , olanzapine
- የንግግር ህክምና ስለ ህመሙ በደንብ እራስን ማስተማር እና ህመሙን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ነገሮችን በመለየት እናሱን መራቅ እንደ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ዮጋ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት እና የመሳሰሉትን የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ማድረግ።
- ኤሌክትሮኮንቮልሲቭ ቴራፒ (ECT)
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.