ዳማከሴDamakese

የባይፖላር ህመም

የባይፖላር ህመም ሥር የሰደደ የስሜት መረበሽ ሲሆን በስሜት፣ በአስተሳሰብ፣ በንቃት እና በባህርይ ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ያደርጋል። ማኒክ እና ሃይፖማኒክ መሆን የበሽታው ዋና ምልክት ናቸው። ባይፖላር ለማከም ከበድ የሚል እና በታካሚው፣ በቤተሰቡ እና በሃገር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና የሚያደርስ ህመም ነው። አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ በባፖላር የመጠቃት 0.5-1% እድል አለው። ሴቶች እና ወንዶች እኩል የመታመም እድል አላቸው። ባይፖላር I እና ባይፖላር II ተብሎ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን፣

  • ባይፖላር I የማኒያ ምልክት ከድባቴ ጋር አንድላይ አርጎ የሚይዝ ሲሆን
  • ባይፖላር II ደግሞ የሃይፖማኒያ ምልክትን ከድባቴ ጋር አንድላይ አርጎ የሚያሳይ ህመም ነው።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።