የደም ግፊት በመለኪያ ተለክቶ ቢያንስ በ4ሰአት ልዩነት እና ከ7ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሁለት ልኬቶች ከ140/90 በላይ ሲሆን የሚከሰት ሲሆን፤ ሽንት ውስጥ የሚኖር የፕሮቲን መጠን በዛ ተብሎ የሚታየው ደግሞ በእርግዝና ጊዜ በ24 ሰአታት ውስጥ ከ300ሚሊ ግራም በላይ ወይም በሁለት የሽንት ናሙናዎች ውስጥ ደግሞ ከ+1 በላይ ፕሮቲን ሲገኝ ነው። ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ግፊት በሽታ ተብሎ የሚወሰደው ከላይ የተጠቀሰው የግፊት ልኬት ከ20ኛው የእርግዝና ሳምንት በኋላ ሲኖር ነው። በመሆኑም ይህ ግፊት ከፕሮቲን በሽንት በብዛት መወገድ ጋር ሲፈጠር ወይንም ደግሞ የግፊት መጠን ከ 160/100 በላይ ሲሆን ፕሪክላምሺያ ተብሎ ይጠራል። ፕሪክላምሺያ ከእርግዝና ጋር የሚመጣ ደም ግፊት የበለጠ ጉዳት የሚያደርስ እና ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልገው ህመም ነው። ነገር ግን ከ20ኛ ሳምንት እርግዝና ወይንም ከወሊድ 12 ሳምንት በኋላ የሚኖር ግፊት ከሆነ ግን ከእርግዝና ጋር የማይገናኝ የደም ግፊት ህመም ተደርጎ ይወሰዳል።
- የመጀመሪያ እርግዝና
- እድሜ ከ20 በታች ወይም ከ40 በላይ መሆን
- በቀድሞ እርግዝና ተመሳሳይ ችግር መኖር
- በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር መኖር
- የመጨረሻ እርግዝና ከ7ዓመት በላይ የራቀ መሆን
- መንታ መርገዝ
- ከመጠን ያለፈ ውፍረት
- ተጓዳኝ እና የቆየ የደም ግፊት እና ስኳር በሽታ መኖር
- ተጓዳኝ የኩላሊት በሽታ ናቸው
ይህ ህመም የተለያዩ የአካል ክፍሎች ላይ አስከፊ ጉዳት ያስከትላል። ምልክቶቹም የሚነሱት እነዚህ አካል ክፍሎች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳቶች ነው።
- በህመም ማስታገሻ የማይመለስ ራስ ምታት
- የጨጓራ መቃጠል
- የሽንት መጠን ማነው ወይንም ቀለም መቀየር
- የፊት እና እግር ማበጥ
- ሳል እና ትንፋሽ ማጠር
እናት ላይ ያለው ጉዳት
- ጭንቅላት ውስጥ የሚኖረው የደም ዝውውርን መረበሽ
- የሳንባ ውሃ መቋጠር
- የልብ መድከም
- የጉበት ጉዳት
- የኩላሊት መድከም
- የምጥ ቶሎ መምጣት
- የሚጥል በሽታ ጽንስ ላይ ያለው ጉዳት
- የጽንስ መቀጨጭ
- የጽንስ ከጊዜው ቀድሞ መወለድ፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፡
- የሳንባ በተገቢው መጠን ያለማደግ
- የስኳር መጠን ማነስ
የደም ሴል መጠን መለኪያ ምርመራ የኩላሊት ምርመራ የጉበት ምርመራ አልትራሳውንድ BPP (የጽንስ ጤና ማጣሪያ ምርመራ)
የጸና ፕሪክላምሺያ ሲኖር የምንከተለው የህክምና መንገድ በጽንሱ እድሜ ላይ ተመርኩዞ ይወሰናል።
- ከ28 ሳምንት በታች ከሆነ ጽንሱን ማቋረጥ
- ከ28-34 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ክትትል ማድረግ እና ጽንሱን የተቻለ ያህል መግፋት ነው
- ከ34 ሳምንት በላይ ባለው ጊዜ ግን እንደ እድገት ደረጃው እና እንደ እናቲቱ ሁኔታ ታይቶ ይወለዳል በመሆኑም አንዳንድ አስከፊ ጉዳቶች ሲፈጠሩ ሃኪሞ የእናቲቱን ህይወት ቅድሚያ በመስጠት ጽንሱ ወዲያው እንዲቋረጥ ሊወስን ይችላል። በተጨማሪ የሚሰጡ ህክምናዎች፡ የጸና ህመም ካለ እና ጽንሱ በማንኛውም ሰአት የመወለድ እድል ካለው
- የሚጥል በሽታን የሚከላከል መድሃኒት - MgSO4
- የጽንሱ ሳንባ እንዲያድግ የሚረዳ መድሃኒት - Dexamethasone
- የግፊት መድሃኒት (የደም ግፊት ከ160/110 በላይ ሲሆን ይሰጣል) Labetalol, Nifedipine , Hydralazine
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.