ዳማከሴDamakese

ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ግፊት በሽታ

የደም ግፊት በመለኪያ ተለክቶ ቢያንስ በ4ሰአት ልዩነት እና ከ7ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሁለት ልኬቶች ከ140/90 በላይ ሲሆን የሚከሰት ሲሆን፤ ሽንት ውስጥ የሚኖር የፕሮቲን መጠን በዛ ተብሎ የሚታየው ደግሞ በእርግዝና ጊዜ በ24 ሰአታት ውስጥ ከ300ሚሊ ግራም በላይ ወይም በሁለት የሽንት ናሙናዎች ውስጥ ደግሞ ከ+1 በላይ ፕሮቲን ሲገኝ ነው። ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ግፊት በሽታ ተብሎ የሚወሰደው ከላይ የተጠቀሰው የግፊት ልኬት ከ20ኛው የእርግዝና ሳምንት በኋላ ሲኖር ነው። በመሆኑም ይህ ግፊት ከፕሮቲን በሽንት በብዛት መወገድ ጋር ሲፈጠር ወይንም ደግሞ የግፊት መጠን ከ 160/100 በላይ ሲሆን ፕሪክላምሺያ ተብሎ ይጠራል። ፕሪክላምሺያ ከእርግዝና ጋር የሚመጣ ደም ግፊት የበለጠ ጉዳት የሚያደርስ እና ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልገው ህመም ነው። ነገር ግን ከ20ኛ ሳምንት እርግዝና ወይንም ከወሊድ 12 ሳምንት በኋላ የሚኖር ግፊት ከሆነ ግን ከእርግዝና ጋር የማይገናኝ የደም ግፊት ህመም ተደርጎ ይወሰዳል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።