ተለምዶ የልብ ድካም ተብሎ የሚጠራው በሽታ የልብ ጡንቻዎ ላይ የደም ዝውውር ባለመኖሩ የሚከሰት እጅግ በጣም አደገኛ ህመም ነው። የደም ዝውውር እጥረት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የልብ ቧንቧዎች በረጋ ደም ከመዘጋቱ ጋር የተያያዘ ነው። ወደ ልብ የሚሄደው ደም ዝውውር ሲቀን የልብ ጡንቻ መድከም እንዲሁም የሴሎቹ ሞት ሊከሰት ይችላል። የልብ ድካም ድንገተኛ ሞት ከሚፈጥሩ በሽታዎች አንዱ በመሆኑ ቀጣይ የሚገለጹት ምልክቶች ከታየቦት **ቶሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣት አለቦት!
- የደረት ሕመም ፡ ደረት ላይ የሚሰማ ምቾት ማጣት ወይም ከባድ ነገር ደረት ላይ የተቀመጠ አይነት ስሜት ነው። ወደ ግራ ክንድዎ (ወይም ሁለቱም ክንዶችዎ)፣ ትከሻዎ፣ አንገትዎ፣ መንጋጋዎ ሊሰራጭ ይችላል።
- የትንፋሽ ማጠር ወይም የመተንፈስ ችግር
- ድካም
- ላብ በላብ መሆን
- ከፍተኛ የጭንቀት ስሜት
- ማዞር እና እራስ መሳት
ሴቶች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎች እና የስኳር በሽተኞች ላይ ምልክቱ ለየት ይላል። ይህም፡
- ማቅለሽለሽ ወይም የሆድ ህመም
- የጨጓራ በሽታ የሚመስል ምልክት ማሳየት
- የልብ ቶሎ ቶሎ መምታት
- የፍርሃት ስሜት
- ላብ በላብ መሆን
- የደም ግፊት በሽታ
- የስኳር በሽታ
- ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት
- ትንባሆ ማጨስ
- ከመጠን በላይ የሆነ የአልኮል ፍጆታ
- ብዙ እንቅስቃሴ የሌለው አኗኗር
- ጾታ፡ ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ይጠቃሉ
- እድሜ በተለይ ከ55 በላይ መሆን
- በቤተሰብ ውስጥ ድንገት በልብ ህመም ከ40 ዓመት በፊት የሞተ ሰው ሲኖር
- ጤናማ አመጋገብ
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- የግፊት እና ስኳር መድሃኒቶችን በትክክል መውሰድ
- በየጊዜው ሃኪም በመጎብኛት ጠቅላላ ምርመራ ማድረግ
- ትንባሆ ያለማጨስ ፣ የአልኮል ፍጆታን መቀነስ
ምልክቶችን ተመልክተው በድንገተኛ ክፍል ህክምናው ወዲያው ሊጀመር ይችላል
- ኢሲጂ
- ኢኮካርዲዮግራፊ
- ትሮፖኒን ተጨማሪ ምርመራዎች እንደ ሃኪሞ ውሳኔ ሊጨመሩ ይችላሉ።
የህክምናው አማራጭ በሃኪሞ እንደበሽተኛው ሁኔታ ይወሰናል። በብዛት የምንጠቀማቸው መድሃኒቶች ቀጣይ ተገልጸዋል።
- oxygen
- asprin
- UFH
- morphine
- nitroglycerin
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.