ዳማከሴDamakese

ልብ ድካም

ተለምዶ የልብ ድካም ተብሎ የሚጠራው በሽታ የልብ ጡንቻዎ ላይ የደም ዝውውር ባለመኖሩ የሚከሰት እጅግ በጣም አደገኛ ህመም ነው። የደም ዝውውር እጥረት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የልብ ቧንቧዎች በረጋ ደም ከመዘጋቱ ጋር የተያያዘ ነው። ወደ ልብ የሚሄደው ደም ዝውውር ሲቀን የልብ ጡንቻ መድከም እንዲሁም የሴሎቹ ሞት ሊከሰት ይችላል። የልብ ድካም ድንገተኛ ሞት ከሚፈጥሩ በሽታዎች አንዱ በመሆኑ ቀጣይ የሚገለጹት ምልክቶች ከታየቦት **ቶሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣት አለቦት!

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።