የጡት ካንሰር በጡት ሕዋሳት ውስጥ የሚፈጠር ካንሰር ነው። የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በጣም የተለመደ ነቀርሳ ነው ከሰድስት ሴቶች አንዷ የመጠቃት እድል አላት። የጡት ካንሰር በወንዶችም በሴቶችም ሊከሰት ይችላል ነገር ግን በወንዶች ላይ የመከሰት እድሉ አናሳ ነው የጡት ካንሰር የመዳን መጠን ጨምሯል፣ እና ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው፣ ይህም የሆነው ስለ ህመሙ ያለው ግንዛቤ በመጨመሩ ፣ ሴቶች ግለ-ምርመራ ማድረግ በመጀመራቸው እና ቶሎ የህክምና አገልግሎት መጠየቅ በመጀምራቸው ነው።
- የእድሜ መግፋት
- ልጅ ያለመውለድ ወይም ጡት ያለ ማጥባት
- የወር አበባ ቶሎ መጀመር እና ዘግይቶ ማረጥ
- በዘር(በቤተሰብ ውስጥ) የጡት፣የማህጸን እና የአንጀት ካንሰር መኖር
- ከመጠን ያለፈ ውፍረት
- ሲጋራ ማጨስ
- የጡት እብጠት
- የጡት መጠን፣ ቅርፅ ወይም ገጽታ ለውጥ
- በጡት ላይ ባለው ቆዳ ላይ ያሉ ለውጦች, ለምሳሌ እንደ መጎድጎድ፣ መቅላት
- የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሰርጎድ
- በጡት ጫፍ ማሳከክ፣መቁሰል፣ እና ከጡት ጫፍ ሚወጣ ፈሳሽ
- ብብት ላይ እብጠት መኖር
ከታች የተጠቀሱት የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ እንዲሁም በጊዜ እንዲገኝ ይረዳሉ
- ጤናማ የሰውነት ክብደት
- ልጅ ከወለዱ ማጥባት
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ግለ ምርመራ ለራስ ማረግ
- ለማረጥ የሚሰጡ ሆርሞኖችን ያለመጠቀም
- ከ50 ዕድሜ በኋላ ማሞግራፊ በየ2 ዓመት ልዩነት በማሰራት ቅድመ ምርመራ ማድረግ
- ከ40-49 ዕድሜ ያሉ ሴቶች ደሞ ቅድመ ምርመራ ለመጀመር ከፈለጉ ሃኪማቸውን ማማከር ይችላሉ
- የጡት አልትራሳውንድ
- ማሞግፊ
- ከእብጠቱ ላይ ናሙና ተወስዶ የሚደረግ ምርመራ አንዴ የጡት ካንሰር ከተገኘ በኋላ መንሰራፋት መኖሩን ለማጣራት
- የደረት ኤክስ ሬይ ወይም ሲቲ ስካን
- የሆድ አልትራሳውንድ ይሰራል
- እንዲሁም የተለያዩ የደም ምርመራዎች ይደረጋሉ
- ቀዶ ህክምና
- ኬሞቴራፒ
- የጨረር ህክምና
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.