Damakese

የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር በጡት ሕዋሳት ውስጥ የሚፈጠር ካንሰር ነው። የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በጣም የተለመደ ነቀርሳ ነው ከሰድስት ሴቶች አንዷ የመጠቃት እድል አላት። የጡት ካንሰር በወንዶችም በሴቶችም ሊከሰት ይችላል ነገር ግን በወንዶች ላይ የመከሰት እድሉ አናሳ ነው የጡት ካንሰር የመዳን መጠን ጨምሯል፣ እና ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው፣ ይህም የሆነው ስለ ህመሙ ያለው ግንዛቤ በመጨመሩ ፣ ሴቶች ግለ-ምርመራ ማድረግ በመጀመራቸው እና ቶሎ የህክምና አገልግሎት መጠየቅ በመጀምራቸው ነው።

This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.