ዳውን ሲንድሮም የሚፈጠረው የዘረግንድ (chromosomes) ቁጥር 21 በተፈጥሮ ሁለት በመሆን ፋንታ ሶስት በሚሆንበት ጊዜ ነው። በመሆኑም ተጠቂ ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ የሚኖሩ እና የአእምሮ አስተዳደግን እና ሌሎች የሰውነት አካላትን የሚያጠቁ የአፈጣጠር ችግሮችን ያስተናግዳሉ። ዳውን ሲንድሮም በአማካኝ ከ 763 ህጻናት አንዱን የማጥቃት እድል ያለው ሲሆን ይህ ቁጥር የእናት እድሜ በሚጨምርበት ጊዜ አብሮ የሚጨምር ነው። ለቤተሰብም ሆነ ለሃገር ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር የሚችል ህመም ሲሆን ተገቢ ግንዛቤ መኖሩ ህጻናቱንም ሆነ ወላጆችን ለደገፍ ይረዳል። በዳውን ሲንድሮም የተጠቁ ህጻናት በ ማካኝ ከ50-55 ዓመት ያህል ይኖራሉ። በአእምሮ እድገት ከሌላው ሰው የዘገሙ ሲሆኑ የምሰጣቸው ትምህርትም ይሄን ያገናዘበ እና ትእግስት የተሞላበት መሆን አለበት በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች እድሜያቸውን ሙሉ ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው ስለሚችል ይህን ማገናዘብ እና ግንዛቤን በመጨመር ይህን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁነት ያስፈልጋል። ለዳውን ሲንድሮም አጋላጭ ሆኖ የተለየው የእናቶች እድሜ መግፋት ነው (በተለየም ደግሞ ከ35 ዓመት በላይ የሚፈጠር እርግዝና)። በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ብዙ ሴቶች የመጀምሪያ ልጆችን የሚወልዱበት እድሜ ከሌሎች ክፍለዘመናት አንጻር እየጨመረ ስለመጣ ዳውን ሲንድሮም የመፈጠሩም እድል ከፍ እያለ ይገኛል። በመሆኑም በርግዝና ግዜ የሚደረጉ የደም እና አልትራሳውንድ ምርመራዎችን በመጠቀም በእርግዝና ግዜ ሳሉ የዳውን ሲንድሮም ተጠቂ የሆነ ጽንስ መኖሩን ማጣራት እና ለወላጆች የጽንስ ማቋረጥ እድልን መስጠት እንደ አማራጭ አለ።
- ትንሽ አፍ
- ዝቅ ያሉ ትናንሽ ጆሮዎች
- በጣም አጭር አንገት
- አንገትን መደገፍ፣ ራስን ችሎ መቀመጥን የመሳሰሉ የእድገት ደረጃዎች መዘግየት
- ትናንሽ እና ያጋደሉ የዓይን ቀዳዳዎች (የኤዣ ዝርያ ላይ የተለመዱ አይነት አይኖች)
- የተለየ የቅንድብ አስተዳደግ
- የዘገየ አካላዊ እድግት
- አማካይ ቁመታቸው የወንዶች 151 ሴሜ ሲሆን የሴቶቹ ደግሞ 141 ሴሜ ነው፣
- ከቁመት ጋር የማይመጣጠን እና የተለቀ ክብደት
- ከውልጃ ጀምሮ የሚኖር የልብ ህመም (ልብ ላይ ቀዳዳ መኖር፣የቫልቭ ችግር፣ የልብ )
- የእይታ ችግር (ግላውኮማ፣ ሞራ)
- የማዳመጥ ችግር (በተደጋጋሚ የሚፈጠር የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የታንቡር ችግር፣ የነርቭ ችግር)
- የሳንባ ችግር(የሚደጋገም የሳንባ ምች፣አስም)
- የአእምሮ እድገት መዝገም
- የሚጥል በሽታ
- የደም ካንሰር
- የእንቅርት በሽታ(ታይሮይድ ማነስ)
- የምግብ ቧንቧ መደፈን ናቸው
- የጆሮ እና አይን ምርመራ
- የልብ አልትራሳውንድ (ኢኮካርዲዮግራፊ)
- የታይሮይድ መጠን ምርመራ
- የደም ሴል መጠን ምረመራ
- ኤክስሬይ
ዳውን ሲንድሮም የማያጠቃው የሰውነት አካል የለም፣ ይህ አሳዛኝ እውነታ ነው። በመሆኑም ወላጆች ስለችግሩ በመረዳት እና ተገቢዎቹን በተደጋጋሚ የሚደርጉ የማጣሪያ ምርመራዎች ለህጻናቱ በማስደረግ ህክምና በሚደርስበት ድረጃ የተገኙትን ችግሮች በመቆጣጠር ለልጆቹ የተሻለውን ያህል የተመቸ አስተዳደግ ለመፍጠር መቻል አለባቸው። እንዲሁም የመማር እና ከሌሎች ልጆች ጋር የመጫወት እድልን መፍጠር፣ ከበሽታው ጋር ተያይዞ የሚመጣው ማግለልን መከላከል ተገቢውን የስነልቦና ድጋፍ ማድረግ መሞከር አለባቸው። ዳውን ሲንድሮም ያለባቸውን ልጆች ከምናግዝበት መንገዶች ውስጥ የተወሰኑት፡
- ለመጀመርያ ጊዜ በልጃችን ሳናፍር ወደ ውጭ ይዘነው ብንወጣ
- አብረን ለመሳቅ፣ ለመጫወት ጊዜ ብንሰጠው
- ካደገ በኋላ አብረን ሁሉንም ነገር ብንከታተለው
- ከአንዱ ስራ ወደ ሚቀጥለው ስራ እንዲገባ ማስለመድ
- ዳውን ሲንድሮም ልጅን እራሱ መርጦ የፈለገውን እንዲያደርግ መተው
- የተለመዱ ትዕዛዛትን አውቆ እንዲሰራ ማገዝ ለምሳሌ ጠዋት ፊቱን፣ ጥርሱን እንዲታጠብ እና ቁርሱን እንዲበላ ልምድ እንዲኖረው ማድረግ፣
- ችግሮችን በራሳቸው እንዲፈቱ ማማከርን ማስለመድ ፣ እንዲያስቡ እገዛ ማድረግ
- በሰው ፊት መጫወት፣ ማውራት፣ ሌሎች ልጆች ጋር እንዲጫወቱ መጋበዝ፣
- ለወላጅ ይህ ህመም የሚያደርሰው ጫና ከባድ በመሆኑም በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያሉ ሌሎች ወላጆችን በማግኘት መደጋገፍ
- መረዳዳት እና የስነልቦና እርዳታ ማግኘት ጫናውን ለመቀነስ ይረዳል።
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.