ዳማከሴDamakese

ዳውን ሲንድሮም

ዳውን ሲንድሮም የሚፈጠረው የዘረግንድ (chromosomes) ቁጥር 21 በተፈጥሮ ሁለት በመሆን ፋንታ ሶስት በሚሆንበት ጊዜ ነው። በመሆኑም ተጠቂ ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ የሚኖሩ እና የአእምሮ አስተዳደግን እና ሌሎች የሰውነት አካላትን የሚያጠቁ የአፈጣጠር ችግሮችን ያስተናግዳሉ። ዳውን ሲንድሮም በአማካኝ ከ 763 ህጻናት አንዱን የማጥቃት እድል ያለው ሲሆን ይህ ቁጥር የእናት እድሜ በሚጨምርበት ጊዜ አብሮ የሚጨምር ነው። ለቤተሰብም ሆነ ለሃገር ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር የሚችል ህመም ሲሆን ተገቢ ግንዛቤ መኖሩ ህጻናቱንም ሆነ ወላጆችን ለደገፍ ይረዳል። በዳውን ሲንድሮም የተጠቁ ህጻናት በ ማካኝ ከ50-55 ዓመት ያህል ይኖራሉ። በአእምሮ እድገት ከሌላው ሰው የዘገሙ ሲሆኑ የምሰጣቸው ትምህርትም ይሄን ያገናዘበ እና ትእግስት የተሞላበት መሆን አለበት በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች እድሜያቸውን ሙሉ ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው ስለሚችል ይህን ማገናዘብ እና ግንዛቤን በመጨመር ይህን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁነት ያስፈልጋል። ለዳውን ሲንድሮም አጋላጭ ሆኖ የተለየው የእናቶች እድሜ መግፋት ነው (በተለየም ደግሞ ከ35 ዓመት በላይ የሚፈጠር እርግዝና)። በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ብዙ ሴቶች የመጀምሪያ ልጆችን የሚወልዱበት እድሜ ከሌሎች ክፍለዘመናት አንጻር እየጨመረ ስለመጣ ዳውን ሲንድሮም የመፈጠሩም እድል ከፍ እያለ ይገኛል። በመሆኑም በርግዝና ግዜ የሚደረጉ የደም እና አልትራሳውንድ ምርመራዎችን በመጠቀም በእርግዝና ግዜ ሳሉ የዳውን ሲንድሮም ተጠቂ የሆነ ጽንስ መኖሩን ማጣራት እና ለወላጆች የጽንስ ማቋረጥ እድልን መስጠት እንደ አማራጭ አለ።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።