DamakeseDamakese

የልጅ እንክብካቤ ድጋፍ ቡድን

እናቶችዬ እንዴት ናችሁ ልጄ 6 ወሯ ነው እስካሁን ቁጭ ማለት አትችልም ጭንቅ ሲለኝ ነው እናንተ ጋር የመጣሁት

5

Yaadota (5)Comments

  • Damakese

    አይዞሽ የኔ ልጅም ቆይቶ ነው ቁጭ ማለት የጀመረው

  • Damakese

    7 ወር ሊጨርስ አካባቢ

  • Damakese

    አንዳንድ ልጆች ይቆያሉ

  • Damakese

    ጎሽ ጭንቅ ብሎኝ ነበር!

  • Damakese

    ሰላም ሚሚ፤ ዳማከሴዎች ነን። የልጆች የእድገት እና መዳበር ፍጥነት የሚለያይ ሲሆን ፤ አብዛኛው ህጻናት በ7ኛ ወር እራሳቸውን ችለው መቀመጥ ይችላሉ። ነገር ግን እስከ 9ወር ባለው ጊዜ ሁሉም ልጆች እራሳቸውን ችለው መቀመጥ እንዲችሉ ይጠበቃል። ይህ ካልሆነ ወደ ህጻናት ሃኪም በፍጥነት መሄድ ይርኖብሻል በተጨማሪም፡ በ7ኛው ወር መጨረሻ ላይ ብዙ ህጻናት ፡ - ከሆድ ወደ ጀርባ እንዲሁም ከጀርባ ወደ ሆድ መገለባበጥ ይጀምራሉ - በእጆጃቸው መካከል እቃን መቀባበል ይችላሉ - ያለድጋፍ በመቀመጫቸው መቀመጥ ይችላሉ - ቀለምን ልቅም አርገው ማየት እንዲሁም ከሩቅ ያለ ነገርን መመልከት ይጀምራሉ - ስማቸው ሲጠራ መለየት እና መዞር ይጀምራሉ - ተመሳሳይ ድምጾችን መደጋገም የጀምራሉ (ለምሳሌ፡ ባ - ባ - ባ- ባ) - መስታወት ላይ መልካቸውን ሲያዩ ትኩረት መስጠት ይምጀራሉ