የስኳር በሽታ የሰውነት ስኳር መቆጣጠር አቅም መዛባት ሲኖር የሚፈጠር ህመም ነው ሰውነታችን ኢንሱሊን ሚባል ሆርሞን በመጠቀም የስኳር ምጠኑን ይቆጣጠራል የዚህ ሆርሞን መጠን ሲቀንስ የስኳር በሽታ ይከሰታል። በህክምና አለም ሁለት የስኳር በሽታ አይነቶች አሉ
- አንደኛው- በህጻናት ላይ አብዝቶ የሚታይ ሲሆን የኢንሱሊን ሙሉበሙሉ ማጠርን ተከትሎ የሚመጣ ነው።
- ሁለተኛው- በአዋቂዎች ላይ በአብዛኛው የሚታይ ሲሆን የኢንሱሊን ስራ መዛባትን ተከትሎ የሚታይ ነው።
- የሰውነት ክብደት ከመጠን በላይ መሆን
- በዘር ተጋላጭ መሆን
- እድሜ መጨመር
- የተወሰነ ብቻ እንቅስቃሴ ያለበት አኗኗር መኖር
ቶሎ ቶሎ ምራብ፤ ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት፤ ቅጥ ያለፈ የውሃ ጥም፤ የሰውነት ክብደት መቀነስ፤ ድካም የስኳር በሽታን ተከትሎ የሚመጡ የጤና ችግሮች እና ምልክቶቻቸው
- የአይን ህመም፤ ብዥታ፣ የእይታ አቅም መገነስ ፣ መጋረድ
- የነርቭ ህመም፤ መደንዘዝ ፣ የማቃጠል ስሜት፣ መቆጥቆጥ፣ ያሰውነት መስነፍ
- የልብ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም፣ ድካም፣ ለሊት ለሊት የሚብስ ማፈን ፣ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣የእግር ማበጥ
- የኩላሊት መድከም፣ የሽንት ቀለም ሻይ መምሰል፣ የፊት እና እግር ማበጥ ፤ ከመጠን በላይ የሆነ ድካም እና ማዞር
- የአንጀት መታወክ፤ ሆድ መንፋት ፣ ድርቀት ፣ ተቅማጥ
- ከላይ የተገለጹት ጉዳቶች ሚፈጠሩት የስኳር መጠን መቆጣጠር ሳይኖር ሲቀር ነው፤ መድሃኒት በአግባቡ በመጠቀም እነዚህን የጤና ችግሮች መከላከል ይቻላል የስኳር መጠን ማነስ የኢንሱሊን አሰራር መዛባት የስኳር መጠንን ከማብዛት በተጨማሪ ምግብ ባልበላንባቸው ጊዜያት የሰውነት የስኳር መጠንን መመንመን ያምጣል፤ ይህም አእምሮ እና አካል ላይ ክፉ የሆነ ጉዳት ያደርሳል፤ ሁሉም የስኳር ታማሚ ምልክቶቹን በማወቅ ቶሎ ስኳር ያለው ፍሳሽ በመውሰድ ጉዳቱን መከላከል አለበት ምልክቶቹም
- የልብ ምት መጨመር
- ላብበላብ መሆን
- የምረበሽ ስሜት
- ማቅለሽለሽ
- ትኩረት ማጣት
- የእይታ ብዥ ማለት ናቸው ይህ ሲፈጠር ታማሚው ከተቻለ የስኳር መጠኑን በመለካት ከ 70 በታች ከሆነ ይህም ካልተቻለ ምልክቶቹህ ተከትሎ 200ሚሊ ያህል ሚሪንዳ ወይም ስኳር ያለው መጠጥ መውሰድ አለበት።
የስኳር መጠን መልኪያ
- በባዶ ሆድ ሚሰራ ምርመራ( Fasting blood glucose)- >126 mg/dl ሲሆን የስኳር በሽታ መኖሩን ይጠቁማል
- በክትትል ላይ ያለ ታካሚ - 100-130 mg/dl ቢሆን ስኳሩ ጥሩ ቁጥጥር ላይ መኖሩን ያሳያል
- Hemoglobin A1C#- ይህ የድም ምርመራ በየ ሶስት ወር ውስጥ ሚደረግ ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ያለውን ቁጥጥር ያሳያል - 6.5% በላይ ሲሆን በሽታው መኖሩን ይጠቁማል
- ክትትል ላይ ያለ ሰው - 7-7.5% አካባቢ ያለ ውጤት ሲያሳይ ጥሩ የቁጥጥር ሁኔታ ላይ መኖሩን ይጠቁማል
- የሽንት እና ደም ምርመራ - ኩላሊት ያልበትን ሁኔታ ለማጣራት፤
- የስኳር በሽታ ሳይታክም በሚዘገይበት ጊዜ ኩላሊት ላይ ጫና ይፈጥራል ይሄን ለማጣራት የተጠቀሰው ምርመራ ይደረጋል
- የአይን ምርመራ(fundoscopy)- በስኳር በሽታ ምክንያት አይን ላይ የተፈጠረ ጫና መኖሩን ለማጣራት በአመት አንድ ጊዜ ቢደረግ የሚመከር ምርመራ ነው
- የአይን ህመም
- የልብ ድካም
- የኩላሊት መድከም
- የነርቭ ችግር
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.