የወባ በሽታ በወባ ትንኝ የሚተላለፍ እና ፕላዝሞዲየም በሚባል በአይን የማይታይ ፕሮቶዞዋ የሚከሰት ህመም ነው። እንደሃገራችን ባሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሞቃታማ አዳጊ ሃገራት ውስጥ ከፍተኛ ወረርሽኝ የሚፈጥር በሽታ ነው። ይህም የሆነው ሞቃታማ እና ረግረጋማ ቦታዎች ለትንኙ መራባት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥሩ ነው። የወባ በሽታን ከሚያስከስቱ ፕላዝሞዲየም አይነቶች የጸና ህመምን የሚያስከስተው ፋልሲፓረም የሚባለው ዝርያ ሲሆን፤ ቫይቫክስ የተሰኘው ደግሞ በየጊዜው የሚቀሰቀስ አይነት የወባ በሽታን በመፍጠሩ ይታወቃል።
የወባ በሽታ የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል፡-
- ከፍተኛ እና በየተወሰነ ሰአታት ልዩነት የሚመላለስ ትኩሳት
- ማንቀጥቀጥ እና ብርድ ብርድ ማለት
- ራስ ምታት
- ሰውነት መቆረጣጠም
- ሆድ ህመም ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ከላይ ከተገለጹት ውጪ ፋልሲፓረም ሚባለው ዝርያ የጸና የወባ ባሽታ ሲፈጥር የሚኖሩ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።
- ራስ መሳት እና የሚጥል በሽታ (አንጎልን ሲያጠቃ)
- ሳል እና ትንፋሽ ማጠር(ሳንባ ላይ ውሃ መቋጠር ሲንኖር)
- አይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን የሽንት ቀለም ሻይ መምሰል እና ተገጋጋሚ የማይቋረጥ ትውከት (ጉበት ላይ በሚከሰት ጉዳት የተነሳ)
- መገርጣት እና ከፍተኛ ድካም(የደም ማነስ) ወዘተ ናቸው። የጸና የወባ በሽታ በእርግዝና ጊዜ እና በህጻናት ላይ የበለጠ ይታያል በመሆኑም የህመሙ ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ ቶሎ የህክምና ታቋማትን በመጎብኘት የከፋ ጉዳትን መከላከል አልቦት።
የወባ በሽታን ለመከላከል ያለን ዋነኛ መንገድ የትንኙን መባዛት መቆጣጠር ነው። ይህም፦
- ረግረግ እና የተቋጠረ ውሃ በሚኖርበት ጊዜ እሱን ማስወገድ
- አጎበርን የመሰሉ በኬሚካል የታከሙ መከላከያዎችን በመጠቀም በትንኙ መነደፍን መቀነስ
- ከፍተኛ የወባ መተላለፍ ያለባቸው ቦታዎች በሚጓዙበት ጊዜ ከሃኪም የሚሰጡ ቅድመ መከላከልን የሚረዱ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገኙበታል።
የወባውን መኖርን ለማጣራ የሚደረግ ፈጣን የደም ምርመራ(RDT) እና በማይክሮስኮፕ(BLOOD FILM) የሚደረግ ምርመራዎች አሉ። በተጨማሪ ወባው በሰውነት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመለየት እና ለማከም በተለይ የጸና ወባ ሲኖር የሚደረጉ ምርመራዎች፡-
- የደም ሴል መጠን መለኪያ ምርመራ
- የሰውነት የስኳር መጠንን መለካት
- የጉበት ጉዳት መኖሩን ሚለይ ምርመራ
- የኩላሊት ጉዳት መኖሩን ማጣሪያ እና የመሳሰሉት እንደ አስፈላጊነቱ በሃኪሞች ይሰጣል።
የወባ በሽታ መድሃኒት እንደ ዝርያው የሚለይ ሲሆን በአሁን ሰአት የሚሰጡት ህክምናዎች ፋልሲፓረም እና ቫይቫክስ የሚባሉትን ዝርያዎች ለማጥፋት የሚሰጡ ናቸ ፋልሲፓረም- COARTHEM (artemether-lumefantrine)+primaquine ቫይቫክስ - chloroquine + primaquine ናቸው። COARTHEM- ማቅለሽለሽ፣ጉበት ላይ ሚኖር ጉዳት፣ አልርጂ(ስውነት ላይ ሽፍታ ማምጣት፣ የከንፈር ማበጥ)፣ የሽንት ቀለም መጥቆር chloroquine- የሚጥል በሽታን መቀስቀስ፣ ራስ ምታት፣ የእይታ መዛባት Primaquine- የቀይ ደም ሴሎች መጠን መቀነስ (ደም ማነስ) የጸና የወባ በሽታ ሲኖር ታካሚዎች ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ይኖርባቸዋል፣ የተለያዩ በደም ስር የሚሰጡ መድሃኒቶችም ይሰጣቸዋል።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.