ዳማከሴDamakese

የወባ በሽታ

የወባ በሽታ በወባ ትንኝ የሚተላለፍ እና ፕላዝሞዲየም በሚባል በአይን የማይታይ ፕሮቶዞዋ የሚከሰት ህመም ነው። እንደሃገራችን ባሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሞቃታማ አዳጊ ሃገራት ውስጥ ከፍተኛ ወረርሽኝ የሚፈጥር በሽታ ነው። ይህም የሆነው ሞቃታማ እና ረግረጋማ ቦታዎች ለትንኙ መራባት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥሩ ነው። የወባ በሽታን ከሚያስከስቱ ፕላዝሞዲየም አይነቶች የጸና ህመምን የሚያስከስተው ፋልሲፓረም የሚባለው ዝርያ ሲሆን፤ ቫይቫክስ የተሰኘው ደግሞ በየጊዜው የሚቀሰቀስ አይነት የወባ በሽታን በመፍጠሩ ይታወቃል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።