የጭንቅት በሽታ የተለያዩ ቅርንጫፎች ያሉት የአእምሮ ህመም ነው። እነዚህም
- ጠቅላላ ጭንቅት
- ኦሲዲ
- ማህበራዊ ጭንቀት
- የአንድነገር ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ጭንቀት
- ፓኒክ ዲሶርደር(ከፍተኛ ፍርሃት) ናቸው።
ምንድነው ጠቅላላ ጭንቀት አንድ ሰው ስለተለያዩ ህይወቱ ላይ የተፈጠሩም ሆነ ሊፈጠሩ ይችላሉ ብሎ ስለ ሚጠረጥራቸው ነገሮች በጥብቅ ቢያንስ ለ6 ወር ሲጨነቅ የሚከሰት ህመም ነው። ሴቶች ሁለት እጥፍ ከወንዶች አንጻር የመጠቃት እድል አላቸው። በአብዛኛው በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚታይ በሽታ ነው። 4% የሚሆነውን የማህበረሰብ አካል የሚያጠቃ ህመም ነው።
- ኖር ኢፒነፍሪን እና ግሉታሜት የሚባሉ ንጥረነገሮች መዛባት
- በዘር የመጋለጥ እድል
- ሳይኮሶሻል ሁኔታዎች ናቸው(አደጋ የሆነን ነገር በትክክል መለየት ያለመቻል)
-
**አጋላጭ ሁኔታው**
ብዙውን ጊዜ በጣም አሳሳቢ እና አስጨናቂ ነገር በታማሚው ህይወት ሲፈጠር እሱን ተከትሎ የሚነሳ ህመም ሲሆን፤ የሚያሰቃይ እና ያልተመቻቸ አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች ላይም በከፍተኛ ደረጃ ይታያል
-
**ምልክቶቹ**
- ከፍተኛ የፍርሃት ስሜት ስለ ሁሉም ነገር ያለማቋረጥ መጨነቅ ጭንቀቱን ማቆም ያለመቻል
- ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት ትንፋሽ ማጠር፣ ማላብ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ መቸገር
- እንቅልፍ ማጣት
- የሰውነት ክብደት መቀነስ
-
**ህክምናው**
- የመድሃኒት ህክምና- Fluoxetine , Sertraline Escitalopram, Amitriptyline
- የንግግር ህክምና- ባህሪይ እና አስተሳስብ ለውጥ ላይ ያተኮረ ህክምና
-
ምንድነው
ኦሲዲ በተደጋጋሚ በሚረብሽ ሁኔታ አንድን ተግባር የማድረግ ሃሳብ ሲመላለስ እና ይህን ተከትሎ ድርጊቱን ማድረግ ነው። ይህ ህመም እንደ አእምሮ ህመም ቢያንስ ለ6 ወራት መቆየት ይኖርበታል። እንደ ሌሎቹ የጭንቀት በሽታዎች ይህም በሃያዎቹ እድሜ ውስጥ በተለየ የሚታይ ሲሆን፤ 2-3% የማህበረስቡን አካል የሚያጠቃ ህመም ነው።
-
መንስኤው
- ኖር ኢፒነፍሪን እና ግሉታሜት የሚባሉ ንጥረነገሮች መዛባት
- በዘር የመጋለጥ እድል
- ሳይኮሶሻል ሁኔታዎች ናቸው(አደጋ የሆነን ነገር በትክክል መለየት ያለመቻል)
-
ምልክቶቹ
- አንድን ነገር አድርግ አድርግ የሚል እና ለመቆጣጠር ከባድ የሆነ ሃሳብ ተመላልሶ ይመጣል ይህ ሃሳብ ድርጊቱን ካላደረጉ የማይተው እና ሌላ ሃሳብ እና ስራን የሚከለክል ነው።
- ታማሚው ያንን ድርጊት ያደርጋል(አብዛኛውን ጊዜ በድግግሞሽ) ሃሳቡን የሚያስቆመው ድርጊቱ መፈጸሙ ብቻ ነው። ድርጊቱን ለማድረግ የማይመች ማህበራዊ ሁኔታ ላይ ቢሆኑም እንዲሁም ድሪጊቱ ተቀባይነት ባይኖረውም ከማድረግ ራሳቸውን መከልንከል የከብዳቸዋል። ለምሳሌ- ታማሚው ምላስህን አውጣ የሚል ሃሳብ ወደ አእምሮው ይመጣል ከዛ ስብሰባ ላይ ያለ ቢሆንም እና ትክክለኛ ምግባር ያለመሆኑን ቢረዳም ይህ ሃሳብ በተድጋጋሚ እየመጣ ስራው ላይ እንዳያተኩር ያረገዋል በስተ መጨረሻም ምልሱን ያወጣል ያኔ ሃሳቡ ያቆማል።
-
ህክምናው
- የመድሃኒት ህክምና - Fluoxetine , Sertraline, Escitalopram, Amitriptyline
- የንግግር ህክምና - ባህሪይ እና አስተሳስብ ለውጥ ላይ ያተኮረ ህክምና ነው።
-
ምንድነው
አንድን ነገር ምክንያታዊ ባልሆነ ሁኔታ ከመጠን በላይ መፍራት ፎቢያ ይባላል። ይህ ፍራቻ ማህበራዊ ኑሮ እና ስራ ላይ ተጽኖ የሚያረግ እና ታማሚውን ከአሰበው ነገር የሚያደናቅፍ ነው። በብዛት ከ7ዓመት እድሜ ጀምሮ የሚታዩ ናቸው።
-
ምልክቱ
ታማሚው ከሚፈራው ነገር ጋር ሲጋፈጥ ከፍተኛ የፍርሃት ስሜት፣ የልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ማላብ ፣ ትንፋሽ ማጠር አይነት ምልክቶች ያሳያል። ምሳሌዎች፤ የእባብ ፍራቻ፣ የአይጥ ፍራቻ፣ የደም ፍራቻ፣ የተዘጉ ቦታዎች መፍራት፣ የንፋስ ፍራቻ ወዘተ ናቸው።
-
ህክምናው
የንግግር እና የመድሃኒት ህክምና ነው።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.