የጉበት ማበጥ ጉበት ላይ መግል መቋጠርን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን በቀዶ ህክምና ዘርፍ በብዛት ከሚያጋጥሙ ህመሞች አንዱ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከ20-40 አመት ያሉ ወንዶችን እና አልኮል አብዝተው ሚጠቀሙ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን። በመንስኤው ተነስተን ልንከፋፍለው እንችላለን። እነዚህም፡
- ባክቴሪያ የፈጠረው የጉበት መግል
- አሜባ የፈጠረው የጉበት መግል
- ሃይዳቲድ ሲስት ናቸው።
- ምንድነው በአንጀት ላይ በተፈጥሮ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ወደ ጉበት ሲገቡ የሚፈጠር ህመም ነው ከዛ በተጨማሪ የቀዶ ህክምናን፣ ሆድ እቃ ላይ የደረሰ ህመምን እንዲሁም የሆድ እና የደም ኢንፌክሽንን ተከትሎ ሊመጣ ይችላል።
- ምልክቶቹ
- የቀኝ ሆድ ክፍል ላይ የሚሰማ ህመም
- ቀኝ ትከሻን ማመም
- ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
- ከፍተኛ ትኩሳት
- ብርድ ብርድ ማለት
- የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን
- ምርመራው
- የደም ሴል ምርመራ
- የሆድ አልትራሳውንድ
- የጉበት ስራን የሚያጣራ ምርመራ
- ህክምናው
- የቀዶ ህክምና
- አንቲባዮቲክ የህክምና አማራጭ በሃኪም ይወሰናል
-
ምንድነው በአሜባ ምክንያት በጉበት ውስጥ መግል ሲቋጠር የሚፈጠር ሲሆን፤ ከ20-40 አመት እድሜ ላይ ያሉ አልኮል ጠጪ ወጣቶችን የበለጠ ያጠቃል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አዳጊ ሃገራት ላይ የበለጠ ይታያል። በአሜባ የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በመጠጣት ይተላለፋል።
-
አጋላጭ ሁኔታዎች
- አልኮል አብዝቶ መጠጣት
- የሰውነት በሽታ መከላከል ሚቀንሱ ነገሮች (ኤች አይ ቪ)
- የምግብ እጥረት
- ምልክቶቹ
- ቀኝ ሆድ አካባቢ የሚሰማ ህመም
- ትኩሳት ብርድ ብርድ ማለት
- ሳል
- ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ እና ተቅማጥ
- የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን
- ምርመራው
- የደም ምርመራ
- የሆድ አልትራሳውንድ
- የሰገራ ምርመራ(አሜባ መኖሩን ለማጣራት)
- የጉበት ስራ ማጣሪያ ምርመራ
- አስከፊ ውጤቶች መግሉ ወደሆድ እቃ እና ሳንባ ሊፈነዳ ይችላል ይህ ሲፈጠር ከፍተኛ እና ትንፋሽ የሚያሳጥር የሆድ ህመም የደረት ህመም፣ ራስ መሳት ሊፈጠር ይችላል። እነዚህ ሲያጋጥሙ ቶሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣት ያስፈልጋል። ካልሆነ እስከሞት የሚደርስ አስከፊ ውጤት ሊደርስ ይችላል።
- ህክምናው መድሃኒት ወይም የቀዶ ህክምና አማራጮች አሉ ይህ የሚወሰነው በሃኪሞት ነው።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.