ቲቢ የሳንባ ኢንፈክሽን አይነት ሲሆን ቲበርኩሎሲስ በሚባል ባክቴሪያ የሚከሰት ህመም ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ከሚባሉ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ነው። በተለይም እንደ ሃገራችን ባሉ አዳጊ ሃገራት ውስጥ ወጣቱን ሃይል አብዝቶ በማጥቃት ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጫና ያደርሳል። ከሌሎቹ የሳንባ ምች አይነቶች የሚለየው፦
- ከፍተኛ ተላላፊነት
- የጸና ህመም መፍጠሩ
- ከሳንባ ውጭ ያሉ የሰውነት አካላትን ማጥቃቱ ወዘት ናቸው
ቲቢ የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ነው፤ በትንፋሽ ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ አቅም አለው በተለይም ደሞ በቅርበት የሚኖሩ ወይም የሚሰሩ ሰዎች መካከል የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ነው የተዘጋ እና በቂ አየር የማያገኝ ቦታ ላይ መገኘት ይህን የመተላለፍ እድሉን በጣም ያሰፋዋል በሽታው በአዳጊ ሃገሮች ላይ መስፋፋቱም ከሰው መጠን መብዛት እና የተፋፋገ የኑሮ ሁኔታው ጋር ያገናኘዋል።
ከላይ እንደተጠቀሰው ቲቢ ሳንባን በዋናነት ያጠቃል ነገር ግን ከሳንባ ውጪ ያሉ የሰውነት አካላትንም የማጥቃት እድል አለው ከሳንባ ውጪ የሚከሰት ቲቢ በተለይ እንደ ኤች አይቪ፣ ካንሰር፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያሉ የሰውነትን የበሽታ መከላከል የሚቀንሱ ተጓዳኝ ህመሞች ያለባቸው ታካሚዎች ላይ በብዛት ይከሰታል።
- የሳንባ ቲቢ፦ ሳል(በብዛት ከ 2 ሳምንት ለበለጠ ጊዜ)፣ አክታ፣ የደረት ህመም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የሰውነት መክሳት፣ ሌሊት ማላብ፣ የምግብ ፍላጎት ማጠር
- የንፍፊት ቲቢ፦ አንገት ላይ ፣ብብት ላይ፣ ሽንጥ ላይ ማበጥ ፣ መክሳት፤ ሌሊት ማላብ፤ የምግብ ፍላጎት ማጠር
- የነርቭ ቲቢ፦ ራስ መሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት አካል መስነፍ፤ የሚጥል ሀመም
- የአንጀት ቲቢ፡- ሆድ መንፋት፣ ቁርጠት፣ ተቅማጥ፣ ድርቀት፣ የምግብ ፍላጎት ማጠር
- የአጥንት ቲቢ፡- የአጥንት ህመም፤ ድካም፤ ማጎበጥ
- ሳል ያለበት ሰው በአቅራቢያ ሲኖር ማስክ መጠቀም
- በቂ ብርሃን እና አየር የሚገባበት ክፍል መጠቀም
- በተቻለ መጠን ብዙ ሆነው የተፋፈነ ሁኔታ ላይ መቀመጥን መሸሽ
- ትንባሆ ከማጨስ መቆጠብ
- ተጓዳኝ በሽታ ሲኖር ተገቢውን ህክምና ማካሄድ
- ጥሩ እመጋገብ በመመገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጠቅላላ ጤናን መጠበቅ
- የደም ምርመራ
- አክታ
- ራጅ(ኤክስሬይ)
- እንደ አጠቃው የሰውነት አካል በሃኪም የሚጨመር ምርመራ
- ለምሳሌ፡ ከንፍፊት እብጠት ላይ የሚወሰድ ናሙና
- የአንጎል ቲቢ ሲሆን ከጀርባ(ህብለሰረሰር) የሚቀዳ ፈሳሽ ምርመራ
- የኩላሊት ቲቢ ሲሆን የሽንት እና የኩላሊት ስራ የሚያጣራ ምርመራ እና
- የመሳሰሉት ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ። ቲቢ የያዘው ታካሚ እንደ ፍቃዱ የኤች አይ ቪ ምርመራ ቢያደርግ ይመረጣል።
የሳንባ ቲቢ ለ6 ወር ያህል በሚሰጡ መድሃኒቶች ይታከማል፤ በመጀመሪያ 2 ወር አራቱም መድሃኒቶች ይሰጣሉ የቀሩት 4 ወራት ላይ ደሞ ሁለት መድሃኒቶች ይሰጣሉ። ከሳንባ ውጪ የሚፈጠር ቲቢ ላይ ተጨማሪ መድሃኒቶች እና ረዘም ያለ የህክምና ጊዜ ሊያስፈልግ ይችላል(ይህን ሃኪሞ ይወስነዋል) Rifampicin፣Ethambutol፣Isoniazid፣Pyrimethamine (ለ2 ወራት) Rifampicin፣Isoniazid(ለ4 ወራት)
የቲቢ መድሃኒት ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው መድሃኒቱን በትክክል እና ያለማቋረጥ መስጠት ላይ ነው። ምክንያቱንም መድሃኒት ማቆራረጥ ባክቴሪያው መድሃኒቱን ተለማምዶ ለህክምና የሚከብድ እና የማይበገር እንዲሆን ያረገዋል። በመሆኑም ይህን ለመከላከል ታካሚዎች መድሃኒቱን በህክምና ተቋማት በመገኘት በጤና ባለሙያዎች እየታዩ እንዲወስዱ ይደረጋል። ይህ በምስክር ፊት የሚሰጥ መድሃኒት (Direct Observation Therapy -DOT) ተብሎ ይጠራል የቲቢ ህክምና የሚወስድ ሰው በ 2 ወር ማለቂያ እንዲሁም በ 5 ኛው እና 6 ኛው ወር ማለቂያ ላይ የቲቢውን መጥፋት ለማጣራት የሚደረግ ምርመራ ይደረግለታል በመሆኑም በ5 እና 6 ኛው ወር ላይ ትቢው ካልጠፋ መድሃኒት የሚቋቋም ቲቢ ሊሆን ስለሚችል እሱን ለማጣራት የሚሆኑ ምርመራዎች ይደረጋሉ። መድሃኒት የሚቋቋም ቲቢ ካለ የሚወሰዱት መድሃኒቶች የሚከተሉት ናቸው።
- 4 Bdq -Mfx-Pto-Cfz-Z-HH-E / 5 Lfx-Cfz-Z-E
- Ethionamide፣ Bedaquiline፣ Prothionamide፣ Levofloxacin፣ Clofazimine፣ Moxifloxacin፣ Pyrizinamide ናቸው።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።