ዳማከሴDamakese

አስም

አስም የአየር ቧንቧ መቀላሉ ሲቆጣ እና አየር እንደልቡ ከሳንባ መውጣት ሲከብድ  የሚፈጠር ህመም ነው። መንስኤው ይህ ነው ብሎ ባይገለጽም ብዙ መንገዶች አስም እንዲፈጠር አስተዋጾ ያረጋሉ። አስም አብዛኛውን ጊዜ በልጅነት የሚጀምር ቢሆንም አዋቂዎች ላይም ሊከሰት ይችላል ለአስም መፈጠር አስተዋጾ ሚያረጉ ብዙ ነገሮች አሉ ከነዚህም ውስጥ፡-

  • በዘር
  • በልጅነት የተደጋገመየ አየር ቧንቧ ኢንፌክሽን(ጉንፋን)
  • አቧራ እና ብናኝ የበዛበት ሁኔታ ላይ መኖር
  • በልጅነት ለከሰል ፤ ለትንባሆ እና ለሌሎች ጭሶች መጋለጥ ይገኙበታል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።