ዳማከሴDamakese

ሳይነስ

ሳይነስ የምንላቸው በአየር የተሞሉ ክፍተቶች በፊት ላይ ይገኛሉ። የጭንቅላትን ክብደት መቀነስ፣ አየርን ማሞቅ እና ድምጽን ማስተካከልን የመሰሉ ስራዎች ያላቸው ሲሆን፤ እነዚህ አካላት በኢንፌክሽን ሲጠቁ ያለውን በሽታ ነው ሳየነስ ብለን የምንጠራው። ሳይነስ በባክቴሪያ ፣ ቫይረስ እንዲሁም አለርጂ ሊፈጠር ይችላል። በልምድ ሳይነስ የምንለው ግን አለርጂክ ሳይነሳይተስን ነው።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።