ዳማከሴDamakese

የድባቴ በሽታ(ዲፕሬሽን)

የድባቴ በሽታ ብዙ ሰዎችን በአለም ላይ ከሚያሰቃዩ የአእምሮ ህመሞች አንዱ ሲሆን ተረጂ በማጣት እና ተገቢውን እርዳታ ባለማግኘት ብዙ ሰዎቸ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ድባቴ አእምሮ ውስጥ የሚገኝ እና የሰውን የስሜት ሁኔታ የሚቆጣጠሩ ሴሮቶኒን እና ኖርኢፒነፍሪን የሚባሉ ንጥረነገሮች (ኒውሮትራንስሚተርስ) ሲዛቡ ወይንም በመጠን ሲቀንሱ የሚፈጠር ህመም ሲሆን። በተለያዩ መንገዶች ድምር ውጤት የሚከሰት ነው እነዚህም፡

  1. ከላይ የተቀሰው የንጥረነገር መዛባት
  2. በዘር የመጋለጥ እድል
  3. ግላዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ናቸው(የሚወዱትን ማጣት፣ ከባድ አስተዳደግ ወዘተ)

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።