ዳማከሴDamakese

ብጉር

በጣም የተለመዱ ከሆኑ የቆዳ ህመሞች አንዱ ሲሆን አብዛኛውን አዳጊ ወጣቶችን የሞያጠቃ ህመም ነው። ቆዳ ላይ ያሉ በጣም ጥቃቅን ቀዳዳዎች ሲዘጉ የሚፈጠር ህመም ሲሆን በተለይም ደግሞ ቅባታማ የሆነ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ላይ በተለየ ይታያል። በአብዛኛው ጊዜ ከቅባት መብዛት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ቢሆንም በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት ብጉርም አለ።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።