የትልቁ አንጀት ካንሰር በትልቁ አንጀት ላይ ያልተፈለገ የህዋሳት እድገት በሚኖርበት ጊዜ የሚፈጠር አሰከፊ ካንሰር ነው። በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ገዳይ ከሆኑ ካንሰሮች አንዱ ነው። ነገር ግን በጊዜ ከተያዘ በቀዶ ህክምና እና ተጨማሪ የህክምና አማራጮች በመታከም የመዳን ጥሩ ተስፋ ያለው ካንሰር ነው። በመሆኑም በጊዜ የሚታዩ ምልክቶችን ማወቅ፣ ያሉትን የቅድመ ምርመራ አማራጮች መጠቀም እና በአጠቃላይ በህመሙ ላይ ያለውን ግንዛቤ መጨመር በሽታው በጊዜ እንዲታወቅ እና እንዲታከ ይረዳል።
- እድሜ መግፋት ፡ የአንጀት ካንሰር በማንኛውም እድሜ ሊከሰት ይችላል። ነገር ግን አብዛኛዎቹ የአንጀት ካንሰር ያለባቸው ሰዎች ከ50 በላይ እድሜ ላይ ያሉ ናቸው። ሆኖም ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ከ50 በታች ያለው እድሜ ላይ ካንሰሩ እየጨመረ መጥቷል።
- አንጀት እጢ መኖር - አብዛኛው የአንጀት ካንሰር ከ እጢ (ፖሊፕ) የሚነሳ ነው።
- የአንጀት መቆጣት(IBD) - አንጀት ላይ የሚኖር ቁስለት የሚያመጣ እና ብዙውን ጊዜ የሆድ ህመም፣ ተቅማጥ እና የሰውነት መክሳት የሚያመጣ ህመም ሲሆን፤ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ለአንጀት ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ከፍ ያለ ነው። በተለይ አልሰሬቲቭ ኮላይተስ የሚባለው የአንጀት መቆጣት አይነት ከፍ ያለ ተጋላጭነት ያመጣል።
- የአንጀት ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ ሲኖር፡ የአንጀት ካንሰር ያለበት ዘመድ መኖሩ የአንጀት ካንሰር የመያዝ እድልን ይጨምራል። የአንጀት ካንሰር ወይም የፊንጢጣ ካንሰር ያለባቸው ከአንድ በላይ የቤተሰብ አባል መኖሩ አደጋውን የበለጠ ይጨምራል። ከ 15-20% አንጀት ካንሰር በቤተሰብ የሚመጣ ነው።
- ዝቅተኛ ስራስር ያለው እና በፋብሪካ የሚመረት ምግብ አብዝቶ መጠቀም እንዲሁም ከፍተኛ የቀይ ስጋ ፍጆታ የአንጀት ካሰርን ተጋላጭነት ይጨምራል።
- አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት።
- ትንባሆ ማጨስ
- አልኮል መጠጣት
አብዛኛውን ጊዜ ምልክቶች የሚታዩት በሽታው ስር ከሰደደ በኋላ ነው። ነገር ግን አስደንጋጭ ምልክቶችን ሲመለከቱ ቶሎ ወደ ህክምና መምጣት የህመሙን የመዳን እድል ሰፊ ያደርገዋል።
- ድርቀት እና ተቅማጥ እየተቀያየሩ መፈራረቅ
- በፊንጢጣ በኩል የሚፈስ ደም
- የሆድ መነፋት፣ ቁርጠት ፣ ፈስ መብዛት እና ምቾት ማጣት
- ሰገራ ካሳለፉ በኋላ የቀረ ነገር ያለ አይነት ስሜት (አንጀት ሙሉ በሙሉ ባዶ ያለመሆን ስሜት)
- ድካም
- ምክንያቱ ያልታወቀ የደም ማነስ
- የሰውነት ክብደት በሃይል መቀነስ
- ፋይበር የበዛበት ፍራፍሬ እና አትክልት መመገብ
- የቀይ ስጋ ፍጆታን መመጠን
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ትንባሆ ያለማጨስ እና የአልኮል ፍጆታን መመጠን
- እንዲሁም ተጋላጭነት የላቸው ሰዎች በቤተሰብ የተያዘ ሰው ሲኖር እና የአንጀት መቆጣት ሲኖር
- ከ45-75 አመት እድሜ ያሉ ሰዎች በየ 5 አመት ልዩነት የሲግሞይዶስፒ
- በየ 10 ዓመት ልዩነት ኮሎኖስኮፒ ቅድመ ምርመራ
- በየ1 ዓመት ልዩነት ደግሞ ሰገራ ውስጥ ደም መኖሩን የሚያጣራ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከ75 ዓመት በላይ የሉ ሰዎች ምርመራውን ለማድረግ ከሃኪማቸው ጋር ተነጋግረው መወሰን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ደሞ ከሃኪማቸው ጋር ቀደም ብለው እና በየምያህል ጊዜ ቅድመ ምርመራውን ያድርጉ የሚለውን መወሰን አለባቸው። እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን አስደንጋጭ ምልክቶች በሚያዩበት ጊዜ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ተገቢ ነው።
- የቀዶ ህክምና
- ኬሞ ቴራፒ
- የጨረር ህክምና
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.