DamakeseDamakese

የራስ ምታት በሽታ

በሁሉም ሰው ህይወት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሚያጋጥም ህመም ነው። ራስ ምታት በሽታ ሳይሆን የበሽታ ምልክት ሲሆን የተለያዩ ህመሞች ምክንያት ሊከሰት ይችላል፤ በመሆኑም አብረው የሚመጡ ለሎች ምልክቶችን አብሮ በማገዘብ የራስምታቱን መንስኤ መለየት ይቻላል። ** ምሳሌዎች**

  • የማጅራት ገትር በሽታ፡- ራስ ምታት፣ትኩሳት፣የአንገት ህመም እና መገተር፣ የንቃት መቀነስ
  • የአእምሮ እጢ፡- ራስ ምታት(የተወሰነ የጭንቅላት አካል ላይ የሚጸና በየጊዜው የሚጨምር) የእይታ መቀነስ፣የሰውነት አካል መስነፍ፣ ክብደት በፍጥነት መቀነስ፣ ሌሎች አካላትን ያጠቃ በሃኪም የተለየ ካንሰር ሲኖር ወደ አንጎል በመንሰራፋቱ ሊከሰት ይችላል።
  • የደም ግፊት በሽታ፡- ማጅራት ላይ የበለጠ የሚሰማ የሚወጥር ራስ ምታት ፣ የታወቀ የደም ግፊት ህመም
  • የደም ማነስ በሽታ- ራስ ምታት+ ማዞር፣ መድከም፣ጆሮ ላይ መጮህ
  • የግላውኮማ በሽታ- ራስ ምታት (ግንባር እና ከአይን ጀርባ በተለየ የሚብስ)+ የእይታ ማቀነስ ከላይ የተጠቀሱት ከራስ ምታት ጋር በአጓዳኝ የሚታዩ ምልክቶች ሲኖሩ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ግድ ነው። ራስ ምታት ከላይ ያሉት ህመሞች ጋር ግንኙነት የሌለው ሆኖ በተደጋጋሚ ታማሚን ሊያስቸግር ይችላል፣ ይህ የሚፈጠረው በአብዛኛው በቀጣዮቹ መስኤዎች የተነሳ ነው።
  • ማይግሬን (migraine headache)
  • ከጭንቀት ጋር የሚገናኝ ራስ ምታት(tension headache)
  • ክለስተር ራስምታት(cluster headache) ሲኖሩ ነው።

Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.