የኩላሊት መድከም ማለት ኩላሊት የሚጠበቅበትን የማጣራት ስራ ለመስራት ሲቸገር የሚፈጠር ህመም ነው። ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ተኪ የማይገኝላቸውን ስራዎች የሚሰራ አካል ነው። አብዛኛው ከልብ የሚወጣው ደም ከሚሄድባቸው አካላት አንዱ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱም ሆነ ከውጭ ወደ ሰውነት የምንወስዳቸውን አላስፈላጊ ንጥረ ነገሮች የሚያጣራ እና የሚያስወግድ አካል ነው። በሃገራችን በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ብዙ ታካሚዎች የዲያሊሲስ አገልግሎት አስፈልጓቸው እርዳታ ሲጠይቁ መመልከት የተለመደ ሁኔታ ሆኗል ስለዚህም ሰለኩላሊት በሽታ የተወሰነ ግንዛቤ መጨበጥ አስፈላጊ ነው።
ኩላሊት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጎድቶ ስራውን ሊያቆም ይችላል፤ ይህን ከሚፈጥሩ ነገሮች ውስጥ፡
- ደጋግሞ ማስታወክ እና ማቀመጥ
- የውሃ ፍጆታ በጣም መጠነኛ መሆን
- የትናንሽ ደም ቧንቧዎች ህመም ይገኙበታል ኩላሊት ረዘም ላለ ጊዜ በተደጋጋሚ ጉዳት በመቋቋሙ የሚፈጠር የስራ ማቋረጥ ሊያጋጥመው ይችላል ይህን ሚፈጥሩ ነገሮች
- የደም ግፊት በሽታ
- የስኳር በሽታ፣
- በዘር የሚከሰት የኩላሊት ህመም
- ኤች አይቪ
- ኤስኤልኢ

* የሽንት መጠን ከመጠን በላይ መጨመር (በቀን ከ3 ሊትር በላይ)
- የሽንት መጠን ከመጠን በላይ መቀነስ ወይም ያለመኖር።
- የሽንት ቀለም መቅላት(ሻይ መምሰል)
- የፊት እና እግር ማበጥ
- ትንፋሽ ማጠር
- የሆድ ህመም
- ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ። ርዘም ያለ የኩላሊት ህመምን ተከትሎ የሚከሰቱ የህመሙ ምልክቶች፤
- የደም ማነስ(መገርጣት ፣ መድከም፣ ማዞር)
- የካልሽየም ማነስን ተከትሎ የሚመጣ የአጥንት ህመም
- የሰውነት መክሳት
- የነርቭ ህመም ይገኙበታል
የኩላሊት ህመምን ሙሉ በሙሉ መከላከል አይቻልም። ነገር ግን አጋላጭ የሆኑትን እንደ ስኳር በሽታ እና የደም ግፊት በሽታ ሲኖሩ በትክክል በመታከም እና በመቆጣጠር የህመሙን የመፈጠር እድል መቀነስ ይቻላል። በተጨማሪም በቀን 2 ሊትር ውሃ መጠጣት እንደ ተቅማጥ እና ትውከት አይነት ህመሞች ሲኖሩ ቶሎ የህክምና እርዳታ መጠየቅ አስፈላጊ ነው።
ኩላሊት የማጣራት አቅሙን ከማጣቱ የተነሳ የሚመጡ አስከፊ ውጤቶች ናቸው፡
- የንጥረነገር መዛባት፡ ለምሳሌ፡ ፖታሺየም የሚባለው ንጥረ ነገር መዛባት ሲኖር የልብ ድካም እና የትንፋሽ ማጠር የከሰታል። የካልሽየም እጥረትን ተከትሎ የአጥንት ህመም እና መድከም እንዲሁም የልም ድካም ሊከሰት ይችላል።
- የልብ ክርታስ መቆጣት፡ ይህን ተከትሎ የደረት ህመም፣ ትንፋሽ ሲስቡ የሚብስ ውጋት፣ እንዲሁም ትንፋሽ ማጠር ይከሰል።
- የአንጀት ስራ መዛባት እና የሆድ ውሃ፡ ሆድ ቁርጠት፣ ተደጋጋሚ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ፣ የምግብ ፍላጎት መጥፋት እና የመሳሰሉትን ምልክቶች ያስከትላል።
- የአእምሮ ንቃት መዛባት፡ የትኩረት መጠን መቀነስ፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ራስ መሳት፣ የሚጥል በሽታን የመሰሉ ምልክክቶች ያሳያል።
- የሳንባ ውሃ መቋጠር፡ ሳል፣ ማፈም፣ የደርት ህመም
- የኩላሊት ስራ የሚያጣራ የደም ምርመራ
- የደም ሴሎች መጠን መለኪያ ምርመራ
- የሰውነት ንጥረ ነገር መለኪያ ምርመራ
- የኩላሊት እና ሆድ አልትራሳውንድ
- ራጅ
- እንደ ኩላሊት ህመሙ መንሰኤ ሌሎች ምርመራዎች በሃኪሞች ሊጨመሩ ይችላሉ።
ኩላሊት የማጣራት አቅሙን ሲያጣ እና የሚከተሉት አስከፊ ውጤቶች ሲከሰቱ ዲያሊሲስ አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል
- የንጥረ ነገር መዛባት (የፖታሺየም መጠን ከ 7 መብለጥ እና በሌሎች ህክምናዎች አልመለስ ማለት)
- በሌሎች ህክምናዎች አልመለስ የሚል የሳንባ ውሃ መቋጠር
- አሲዶሲስ
- በዩሪያ መብዛት የመጣ የአእምሮ ንቃት መዛባት እና የልብ ህመም ከዚህ ውጭ የሚደረጉ ህክምናዎች በኩላሊት ህመም ምክንያት የመጡ ምልክቶችን ማከም እና እንደ የደም ግፊት ያሉ የኩላሊት ድክመትን እያባሱ የሚመጡ ትጓዳኝ ህመሞችን ማከም ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.