ኮሎስቶሚ በቀዶ ጥገና ወቅት የሚሠራ አንጀትን በሆድ ግድግዳ ቀዳዳ በማስወጣት የሚሰራ ህክምና ነው። ብዙውን ጊዜ የሚያስፈልገው አንጀት በትክክል እንዳይሰራ የሚያደርግ ህመም ሲኖር ነው። ለምሳሌ- የአንጀት ካንሰር፣ አንጀት ካይ የተፈጠረ ጉዳት(በእንስሳ መወጋት)፣ የአንጀት ቀዶ ህክምና ከተሰራ በኋላ አንጀትን ለማሳረፍ፣ የሰገራ ቁጥጥር ማጣት ሲኖር ወዘተ። ኮሎስቶሚ ሲኖር እንዴት መንከባከብ እንዳለብን ማወቅ ካላስፈላጊ አስከፊ ጉዳቶች ይጠብቃል።
- ተቅማጥ
- የአንጀት መዘጋት
- የወጣው የአንጀት ክፍል ማበጥ
- የቀረው የአንጀት ክፍል ከወጣው አጠገብ አፈንግጦ መውጣት
- የወጣው የአንጀት ክፍል ወደ ሆድ መመለስ
- አካባቢ ላይ ያለ ቆዳ መቆጣት
- የወጣው የአንጀት ክፍል ላይ የሚኖር የደም ዝውውር ማጠር
በወጣው የአንጀት ክፍል ዙሪያ ያለውን ቆዳ መንከባከብ ይህም የሚሆነው፡
- ትክክለኛ አፈሙዝ ያለው ኮሎስቶሚ በመጠቀም
- የሰገራ ማስወገጃውን ከረጢት በየጊዜው በመቀየር
- የሰገራ ማምለጥ እና በአካባቢ ያለውን ቆዳ መንካት ለመከላከል ከሚያስፈልገው ጊዜ በላይ አስሬ ፕላስቲኩን ከማንሳት መቆጠብ
- በዙሪያ ያለውን ቆዳ በውሃ ማጽዳት
የሰገራ ማስወገጃ ከረጢት በየጊዜው መቀየር ይህም የሚደረገው፡
- የሰገራ ማስወገጃ ከረጢቱ ከ1/3 እስከ 1/2 ያህል ሲሞላ እንጀትን እንዳይጎተት እና እንዳይፈስ መቀየር።
- ሲቀይሩ ከመጸዳጃ ቤት ቅርብ በሆነ ቦታ ሆነው ቢሆን ይመረጣል
- የከረጢቱን ታች ወደ ላይ ያዙት እና ክሊፑን ከከረጢቱ ጫፍ ላይ ይክፈቱት።
- ሽንት ቤት ውስጥ ሰገራውን መድፋት
- የከረጢቱን ውስጥ በደንብ ማጽዳት
- ከረጢቱን መች እንቀይር የሚለው እንደ አይነቱ የሚለያይ ቢሆንም እንኳን በአብዛኛው በየ3 ቀን የሚቀየሩ አይነቶች በገበያ ላይ ይገኛሉ።
- ከረጢቱን ለመቀየር ካሰቡ በብዛት በጠዋት ከምግብ በፊት ቢደረግ ይመከራል
- ሙቀት እና ማላብ ሲኖር ከረጢቱ በቀላሉ ከአንጀት ላይ ስለሚላቀቅ ቶሎ ቶሎ መቀየር ሊኖርብን ይችላል።
- ገላዎን በሚታጠቡ ጊዜ የኮሎስቶሚውን አካባቢ በውሃ ብቻ ማጥብ ይገባል። አካባቢው ያለውን ቦታ በሳሙና መታጠብ ከረጢቱ እንዲላላ እና ሰገራ ወደአካባቢው እንዲፈስ ሊያደርግ ይችላል።
- ኮሎስቶሚ ሲጻዳ አንዳንዴ የደም ጠብታ ሊኖር ይችላል። ይህ የሚያሳስብ እይደለም ነገር ግን የበዛ የደም መፍሰስ ካለ ወደ ሃኪሞ ቶሎ መምጣት አለቦት።
- በፈስ መብዛት መቸገር አብሶ መጀመሪያ አካባቢ ሊኖር ይችላል ይህን ለመከላከል በተመሳሳይ ሰአት እነስ ያለ የምግብ መጠን በቀን ከ4-5 ጊዜ መብላት ይረዳል
- የሽታ ችግር ካጋጠሞት ከረጢቱ በደንብ መዘጋቱን ማጣራት ይኖርቦታል በተጨማሪ ቶሎ ቶሎ ከረጢቱን ማጽዳት፣ እንደ እንቁላል፣ ጥቅል ጎመን፣ አይብ ያሉ ምግቦችን መቀነስ ይረዳል።
ቀጣይ ያሉት ምልክቶች ካጋጠሞት ሃኪሞን ቶሎ ያግኙ
- ከ2 ወይም 3 ሰዓታት በላይ የሚቆይ ቁርጠት
- የማያቋርጥ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
- ከቁርጠት እና ከማቅለሽለሽ እብሮ ከ4 እስከ 6 ሰአታት ምንም ሰገራ ካልወጣ
- ከ 5 ወይም ከ 6 ሰአታት በላይ የሚቆይ የበዛ የውሃ መሳይ ፈሳሽ ሲኖር
- ከአንድ ሳምንት በላይ የሚቆይ መጥፎ ሽታ (ይህ የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል)
- በአንጀት ላይ የሚደርስ ጉዳት ሲኖር
- መጥፎ የቆዳ መቆጣት ወይም መቁሰል
- ከቦታው የበዛ ደም መፍሰስ ሲኖር
- በስቶማዎ መጠን ወይም ቀለም ላይ ያልተለመደ ለውጥ ሲኖር ናቸው
Odeeffannoon kun hubannoof qofa; gorsa doktoraa hin bakka bu'u.