የደም ግፊት በሽታ ልብ ደምን የሚገፋበት ሃይል ከምጠን በላይ ከፍ ሲል የሚከሰት ነው። አንድ ሰው በግፊት መለኪያ መሳርያ ከ 140/90 በላይ ሲያስቆጥር ግፊቱ ከፍ ብሏል ተብሎ ዪወሰዳል። ተላላፊ ካልሆኑ እና በወቅቱ በአለም ጤና ድርጅት አሳሳቢ ተብለው ከሚቆጠሩ ህመሞች መካከል አንዱ ነው።
- በእድሜ 40 አመት በላይ መሆን
- ትንባሆ ማጨስ
- ከመጠን በላይ የሆነ የአልኮል ፍጆታ
- ከልክ ያለፈ ውፍረት
- በቤተሰብ ውስጥ ያለ ሰው በግፊት መያዝ
- ተጓዳኝ የስኳር በሽታ እና የስባት መብዛት
- የኩላሊት በሽታ
የደም ግፊት በሽታ በተላያዩ የሰውነት አካላት ላይ በሚያመጣው ተጽኖ ምክንያት የሚፈጠሩ ምልክቶች ያሉት ሲሆን እነዚህም
- የልብ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም፣ ድካም፣ ለሊት ለሊት የሚብስ ማፈን ፣ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣የእግር ማበጥ
- የኩላሊት መድከም፣ የሽንት ቀለም ሻይ መምሰል፣ የፊት እና እግር ማበጥ ፤ ከመጠን በላይ የሆነ ድካም እና ማዞር
- የነርቭ በሽታ(ስትሮክ)፤ እራስ መሳት፣ ግማሽ የሰውነት አካልን ማዘዝ መቸገር የሽንት እና ሰገራ ቁጥጥር ማጣት
የደም ግፊት በሽታ አብዛኛውን የሰውነት አካል ማጥቃቱ አስፈሪ ህመም ቢያረገውም እንኳን መድሃኒቱን በትክክል በመውሰድ እና በሃኪም የሚነገሩ የአኗኗር ለውጦች በማድረግ ህሉንም ጎንዮሽ ጉዳቶች መቅረፍ ይቻላል ፤ ይህም የታማሚውን ቁርጠኝነት እና ከሃኪም ጋር አብሮ መስራትን ይጠይቃል
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ጤናማ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ
- ስባት እና ጨውን በተመጠነ መጠን መጠቀም
- ትንባሆ እና አልኮል ያለመጠቀም
- በየጊዜው የጤና ሁኔታን መከታተል
የልብ ድካም የኩላሊት መድከም የነርቭ በሽታ(ስትሮክ)
የሽንት እና ደም ምርመራ ኩላሊት ያልበትን ሁኔታ ለማጣራት ግፊት እና ኩላሊት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው የደም ግፊት በሽታ ሳይታክም በሚዘገይበት ጊዜ ኩላሊት ላይ ጫና ይፈጥራል ይሄን ለማጣራት የተጠቀሰው ምርመራ ይደረጋል። ኢሲጂ (ECG) - በደም ግፊት የተነሳ ልብ ላይ የደረሰ ችግር መኖሩን ለማጣራት የሚደረግ ምርመራ ነው። እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራዎች በሃኪሞ ሊላኩ ይችላሉ።
- የአኗኗር ለውጥ ማድረግ ይህም፡ ጤናማ አመጋገብ መከተል
- ጨው ያለመጠቀም ወይም በተመጠነ መልክ መጠቀም
- አካል ብቃት እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ፣ ትንባሆን ያለማጨስ
- የሚጠጡትን አልኮል መጠን መቀነስ በአብዛኛው የሚታዘዙ መድሃኒቶች Amlodipine Hydrochlorothiazide Enalapril
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.