ከማህፅን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና የዳበረ እንቁላል ከማህጸን ግድግዳ ውጭ መተከል ነው።
በማህጸን እና ጽንስ ውስጥ ከሚፈጠሩ ድንገተኛ እና አስደንጋጭ ህመሞች አንዱ ነው።
95% ያህል ግዜውን በእንቁላል ማስተላለፊያ ትቦ ውስጥ ይተከላል የቀረው 5% ጊዜ ግን
ሆድ እቃ ውስጥ፣ እንቁልጢ ላይ፣ የማህጸን በር ላይ እና ከዚህ በፊት ኦፕሬሽን የተሰሩ
ሴቶች ላይ ደግሞ የዛ ጠባሳ ላይ ሊፈጥር ይችላል።
በአማካኝ 1.6% እርግዝና ላይ የመፈጠር እድል አለው።
ከ2-3% ከእርግዝና ተያይዘው የሚመጡ ሞቶችን ይፈጥራል።
- የአባላዘር በሽታዎች
- በእንቁላል ማስተላለፊያ ትቦ ላይ የሚደረጉ ቀዶ ህክምናዎች
- ሲጋራ ማጨስ
- የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንክብል(ፖስት ፒል)
- የወር አበባ መቅረት
- በማህጸን የሚወጣ ደም መፍሰስ
- የሆድ ህመም
- የእርግዝና ምልክቶች፡ ማቅለሽለሽ፣ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
- የቱቦው መፈንዳት ሲኖር ደሞ፡ ከፍተኛ የሆድ ህማም፣ ትከሻ ላይ የሚሰማ ህመም፣ፌንት መጣል፣ መገርጣት እና የልብ ቶሎ ቶሎ መምታትን የመሰሉ ምልክቶች ይታያሉ።
- የደም ሴል መጠን መለኪያ ምርመራ
- እርግዝና ማረጋገጫ የሽንት ምርመራ
- አልትራሳውንድ
- መድሃኒት(Methotrexate) መጠቀም፡ ይህ አማራጭ የጽንሱ መጠን ከ3.5ሴሚ በታች ሲሆን ታካሚው ፈቃድ ሲሰጥ፣ ጠቅላላ የታካሚው ሁኔታ አስተማማኝ ሲሆን የጉበት እና የኩላሊት ጤና አስተማማኝ ሲሆን እና በማህጸን ውስጥ ምንም አይነት ጽንስ እንደሌለ ከተረጋገጠ በኋላ የሚወሰድ አማራጭ ነው። Methotrexate ከባድ እና ብዙ የሰውነት አካላት ላይ ተጽኖ የሚያደርስ መድሃኒት ነው ከነዚህም ውስጥ፣ የኩላሊት፣ የሳንባ እና ጉበት ተጽኖው ተጠቃሽ ናቸው። ስለሆነም በጥንቃቂ እና ከቅድመ ምርመራ በኋላ የሚሰጥ መሆን አለበት።
- የቀዶ ህክምና አማራጭ ከላይ ያሉትን መስፈርቶች ለማያሟሉ ታካሚዎች የሚወሰድ ነው። ከማህጸን ውጭ የሚኖር እርግዝና ከ10-20% የመደገም እድል ስላለው ይህ ያጋጠማቸው ሴቶች የወር አበባ መዘግየት እና ለሎች የእርግዝና ምልክቶች ሲኖሩ ፈጥነው ወደ ሃኪም በመምጣት እርግዝናው ከማህጸን ውጪ ያለመሆኑ መጣራት አለበት።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.