የአይን ነርቭ ላይ ጉዳት በማድረስ የእይታን የሚቀንስ ብሎም የሚያወር በሽታ ሲሆን በዓለም ላይ የእይታ መታወር ከሚያስከስቱ የአይን ህመሞች ዋነኛው ነው። ግላውኮማ አይን ውስጥ ያለ ግፊት ከተለመደው በላይ ከፍ ሲል የሚከሰት ህመም ነው። በአይን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ከመጠን በላይ ሲመረት ወይም ዝውውሩ ላይ ችግር ሲኖር የሚከሰት ህመም ነው።
- የደም ግፊት በሽታ
- የስኳር በሽታ
- በቤተሰብ የግላውኮማ ተጠቂ ሰው ካለ
- የቅርብ ወይም የሩቅ እይታ ችግር ካለ
- ከዚህ በፊት የአይን ቀዶ ህክምና አርገው ካወቁ
- የአይን ህመም(ግፍት የሚያረግ ስሜት)
- ራስ ምታት
- የእይታ መጋረድ (እንደ ትቦ መሃል ላይ ያል እይታ ሳይጎዳ ዳር እና ዳር ላይ ያለው እይታ መቀነስ በተለይ ህመሙ ሲጀማምር ይታያል)
- ማቅለሽለሽ
- የአይን መቅላት
ግላውኮማን መከላከል ባንችልም እንኳን ቅድመ መርመራዎችን በማድረግ በጊዜ በማግኘት እና በመታከም የእይታ ማጣትን መከላከል ይቻላል።
- 40-54 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በ1-3 ዓመት ልዩነት
- ከ55-65 ዓመት እድሜ ያላቸው ሰዎች ደሞ በየ 1-2 ዓመት ልዩነት ቅድመ ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል።
- በተጨማሪም ደሞ ለግላኮማ አጋላጭ የሆኑ እንደ ስኳር እና ግፊት ያሉ ህመሞችን በትክክል መታከም አንድ የመከላከያ አማራጭ ነው።
- የእይታ መታወር
- እሱን ተከትሎ በታካሚው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ግላዊ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጠራል።
- የአይን ውስጥ ግፊት መለካት የሚያስችሉ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም መለካት።
- የእይታን አቅም መለካት
- እንደታካሚው ሁኔታ በሃኪሞች ተጨማሪ ምርመራዎች ይታዘዛሉ።
- መድሃኒቶች(ጠብታ መጠቀም)- LATANOPROST , TIMOLOL
- የጨረር ህክምና
- የቀዶ ህክምና ያሉት አማራጮች ሲሆኑ ታካሚው እና ሃኪሙ በጋራ የሚወስኑት ይሆናል።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.