Damakese

የጽንስ መጨናገፍ(ውርጃ)

የጽንስ መጨናገፍ ጽንሱ በድንገት ከ28ኛው የእርግዝና ሳምንት በፊት መቋርጥ ነው። ከ10-20% እርግዝናዎች ድንገት ይቋረጣሉ። ብዙ ጊዜ እርግዝና የሚጨናገፈው በጣም በጊዜ ነው ይህም እናቲቱ እርጉዝ መሆኗን እንኳን ሳታውቅ ሊሆን ይችላል። የእርግዝና መጨናገፍ ብዙ ሴቶችን ሊያጋጥም ቢችልም እንኳን ለሁሉም ሴት በጣም ከባድ የሆነ እና ከፍተኛ የአእምሮ ጫና የሚያደርስ ክፉ አጋጣሚ ነው።

This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.