ስኳር የሰውነት ኢንሱሊን መጠን ሲያንስ ወይንም ስራውን በትክክል መስራት ሲከብደው የሚፈጠር በሽታ ነው። በመሆኑም በእርግዝና ግዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ስኳር መኖሩ ሲረጋጋጥ ከእርግዝና ጋር ተያይዞ እንደመጣ ይወሰዳል። በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም በእርግዝናዎ እና በልጅዎ ጤና ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር የደም ስኳር መጠን ይጨምራል። በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር በሽታ ካለብዎ በአጠቃላይ የደምዎ ስኳር መጠን ከወሊድ በኋላ ወዲያውኑ ወደ መደበኛው ደረጃ ይመለሳል ነገር ግን በእርግዝና የሚከሰት የስኳር ህመም ካለብዎ ለአይነት 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል። ስለዚህ የስኳር ምርመራን በተደጋጋሚ በማድረግ አይነት 2 የስኳር በሽታ ያለመከሰቱን ማጣራት ያስፈልጋል።
- እድሜ ከ35 በላይ መሆን
- ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት
- የቀድሞ እርግዝና ላይ ተመሳሳይ ህመም መኖር
- ከ4ኪሎ በላይ የሆነ ልጅ ከዚህ በፊት መውለድ
- ከባድ እና የተወሳሰብ ወሊድ ከዚህ በፊት ሲኖር
- በቤተሰብ ውስጥ በስኳር የተጠቃ ሌላ ሰው መኖር
- መንታ ማርገዝ ናቸው።
በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የስኳር በሽታ በብዛት ምልክት ላያሳይ ይችላል። በመሆኑም አብዛኛውን ጊዜ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ እናቶች ምርመራ ሲደረግላቸው ይገኛል
- ቶሎ ቶሎ መራብ
- ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት እና ውሃ መጠጣት
- ድካም
- የሰውነት መክሳት
- እናት ላይ
- የወሊድ ያለጊዜው እና በቀዶ ህክምና መቋረጥን ተከትሎ የሚመጡ አስከፊ ጉዳቶች፡
- ከወሊድ በኋላ ያለ ህመም
- የደም መርጋት
- ኢንፌክሽን
- የምጥ መርዘም እና መስተጓጎል(የልጁ ክብደት ከፍተኛ ከሆነ ምጥ ሊስተጓጎል እና ሊቋረጥ ይችላል)
- የሽርት ውሃ መብዛት
- ተያይዞ የሚፈጠር የደም ግፊት በሽታ
- ልጅ ላይ
- ክብደቱ ከፍ ማለት፣ ሲወለድ የስኳር መጠኑ ማነስ፣ የሳንባ አለመብሰል(ማደግ)፣
- በተፈጥሮ የሚመጣ የልብ ክፍተት፣ የጀባ መከፈት ወይም አፈጣጠር ችግር
- የጨቅላው ሰውነት ቢጫ መሆን
- የቀይ ደም ሴል መጠን ከተገቢው በላይ መብዛት ይገኙበታል።
- ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ እናቶች ለክትትል ሲመጡ ወዲያውኑ ለበሽታው ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል።
- ከፍትኛ ተጋላጭነት ለሌላቸው እናቶች ግን ከ 24-28 ሳምንት ውስጥ ምርመራው ይሰራል።
- ምርመራው(OGTT) ከ8-14 ሰአታት ከተጾመ በኋላ የሚሰራ ምርመራ ነው። ከመብላት በፊት እንዲሁም 75 ግራም ግሉኮስ ከተሰጠ በኋላ የስኳር መጠንን በ1 እና 2 ሰአት ልዩነት በመለካት የሚሰራ ምርመራ ነው።
- በተጨማሪ የhgbA1C ምርመራ (ከእርግዝና በፊት የነበረ የስኳር በሽታ ያለመኖሩን ለማጣራት) ይደረጋል።
- የአመጋገብ ማስተካከያ ለማረግ ተገቢውን ትምህርት ለእናቲቱ መስጠት
- መተው/መቀነስ ያለቦት ምግቦች
- ድንች፤ ፓስታ፤ ዳቦ፤ መኮረኒ
- ስኳር የበዛበት መጠጥ፤ ጨው፤ አልኮል
- የሚበረታቱ ምግቦች፡
- ጎመን፤ ሰላጣ፤ ፍራፊሬ
- ጥራጥሬ፤ እንጀራ፤ ብቂ ውሃ መጠጣት።
- የስኳር መጠኑ በአመጋገብ ካልተስተካከለ ኢንሱሊን መጀመር
- እርግዝናውን እና የጽንሱን እድገት በቅርብ መከታተል
- የጽንስ መቋረጫ ጊዜው በሃኪም ሲወሰን ማዋለድ
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.