የጉበት ቫይረስ ጉበትን ከሚያጠቁ እና ስራውን መስራት እንዲከብደው ከሚያረጉ በሽታዎች አንዱ ነው። ጉበትን ለይተው በዋናነት የሚያጠቁ ቫይረሶች አሉ እነሱም፡- Hepatitis A,B,C,D,E(ሄፓታይተስ) ተብለው ይጠራሉ። ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ጉበት ላይ የሚያደርሱት ሄፓታይተስ B እና C ናቸው። ሄፓታይተስ B በሃገራችን እንዲሁም በአለም በአስጊ ሁኔታ እየጨመረ ስለሆነ HBV ላይ ትኩረት እንሰጣለን።
- ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት
- ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍ ይህም የእርግዝና ክትትል ያለመኖር እና ቀድሞ ያለመርመር የሚፈጥረው ነው
- በደም ንክኪ
- በደም ስር የሚወሰዱ አደንዛሽ እጾች
- የሆድ ህመም(በተለይ በቀኝ በኩል)
- ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
- ትኩሳት
- የእይን እና ሰውነት ቢጫ መሆን
- የሽንት ቀለም ሻይ መምሰል
- ድካም እና መገጣጠሚያን መቆረጣጠም
- ስለታማ ነገሮችን አለመጋራት
- የደም ንክኪን ማስወገድ
- ጥንቃቄ የተሞላበት የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ(ኮንዶም መጠቀም)
- በእርግዝና ጊዜ የቫይረሱን መኖር የሚያጣራ ምርመራ ማድረግ
በጉበት መድከም ምክንያት የሚከሰቱ አስከፊ ውጤቶች
- ሆድ ውስጥ ውሃ መቋጥጠር
- ራስ መሳት፣ የንቃት መጠን መቀነስ
- ከላይኛው የአንጀት ክፍል መደድማት (ደም ማስታወክ)
- የኩላሊት መድከም
- የጉበት ካንሰር
- የደም ምርመራ፣ ቫይረሱ መኖሩን የሚያጣራ ምርመራ(HBSAG, HBEAG)፣
- ደም ውስጥ ቫይረሱ ምን ያህል እንደሆነ የሚያጣራ ምርመራ(Viral Load)
የሰውነት ንጥረነገሮ መዛባት መኖሩን የሚያጣራ ምርመራ፣ የኩላሊትን ጤና የሚያጣራ የደም ምርመራ - የሆድ አልትራሳውንድ(ጉበት ላይ ጠባሳ መኖሩን እንዲሁም ሆድ ውስጥ ውሃ መቋጠሩን የሚያጣራ ምርመራ ነው)
እንደ ቫይረሱ መጠን( Viral Load) በሃኪም መድሃኒት ይጀመር ወይ የሚለው ይወሰናል። ይህ ከተደረገ በኋላ የሚታዘዙት መድሃኒቶች Tenofovir እና Entecavir የመሳሰሉት ናቸው። የጉበት መድከም ካለ በምልክቱ ላይ በመነሳት የተለያዩ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። ሃኪሞ መድሃኒት ለመጀመር ካልወሰነ ግን በየ 6 ወር ልዩነት ክትትል በማድረግ የቫይረሱን ደረጃ እና ጉዳት መከታተል ይቻላል።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.