ትርፍ አንጀት የምንለው በተፈጥሮ የትልቁ አንጀት ላይ ተንጠልጥሎ የሚገኝ እና ይህ ነው የሚባል አገልግሎት የሌለው አካል ነው። የትርፍ አንጀት በሽታ የምንለው ትርፍ አንጀት ላይ ኢንፌክሽን ሲፈጠር የሚከሰት ህመም ነው። በአብዛኛው ከሃያዎቹ መጀመሪያ እስከ ሰላሳ ዕድሜ ክልል ላይ የሚታይ በአብዛኛው የሚታይ ህመም ነው። ይህ ህመም የሚከሰተው ትርፍ አንጀት በደረቀ ሰገራ፣ የአንጀት ትላትል እና ሌሎች የአንጀት አካላት ሲዘጋ ነው።
- ከፍተኛ የሆድ ህመም(መጀመሪያ እንብርት አካባቢ የሚነሳ ነገር ግን በጊዜ ሂደት ወደ ዝቅ ብሎ እና በቀኝ በኩል የሚገኘው የሆድ ክፍል የሚሰማ ህመም ህመሙ ታካሚው ሲንቀሳቀስ ወይም ሲያስል ይብሳል።
- ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
- ትኩሳት
- የምግብ ፍላጎት ማጣት
- የደም ምርመራ
- አልትራሳውንድ
- ኤክስሬይ
- የሰውነት ንጥረነገርን ሚለካ ምርመራ ናቸው።
- የትርፍ አንጀት በሽታ ሳይታከም ከቆየ የትርፍ አንጀት ሊፈነዳ ይችላል። ይህ ሲፈጠር የሆድ እቃ ኢንፌክሽን ይከሰታል እሱን ተከትሎ የሚመጡ ምልክቶች፡
- ከፍተኛ እና የማያፈናፍን ሁሉንም የሆድ ክፍል የሚያጠቃ የሆድ ህመም
- ከፍተኛ ትኩሳት፣
- ድካም
- ትንፋሽ ማጠር እናልብ ቶሎ ቶሎ መምታት ናቸው።
- የትርፍ አንጀት መግል መያዝ
- በደም ወደ ሌላ የሰውነት አካል የሚንሰራፋ ኢንፌክሽን
የትርፍ አንጀትን በቀዶ ህክምና ማስወገድ ነው። ነገር ግን እንደ ሃኪም ውሳኔ በደም ስር የሚሰጥ አንቲባዮቲክ እየተሰጠ ታካሚው የተወሰነ ጊዜ ሊቆይ ይችላል።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.