ተቅማጥ እንደ የዓለም ጤና ድርጅተ ገልፃ በቀን ውስጥ 3 ወይም ከዚያ በላይ የላላ ወይም እንደውሃ የቀጠነ ሰገራ ማሳለፍ ነው። ወይም በቀን ውስጥ ከ200 ግራም በላይ ሰገራ ማሳለፍ ነው። ህጻናትን በተለይም ከ9 ወር እስከ 2 ዓመት እድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከሚያጠቁ እና በፈሳች መጠን መራቆት እስከ ሞት ከሚያደርሱ ህመሞች እንዱ ነው። በተለይ በደሃ ሃገራት የህጻናት ሞት ምክንያቶች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው። ተቅማጥ በአብዛኛውን ጊዜ አንጀትን በሚያጠቁ ኢንፌክሽኖች የሚከሰት ነው።
- የእናቶች መጥፎ ልምድ( በመጀመሪያብ 6ወራት ከጡት ወተት ውጪ የሆነ ነገር መስጠት
- ለመጀምሪያ 2 ዓመታት ሙሉ ጡት ያለማጥባት
- ንጽህናን ያለመጠበቅ
- ከማጥባት በፊት እና በኋላ እጅ ያለመታጠብ ይገኙበታል)
- የበሽታን መከላከል የሚቀንሱ ተጓዳኝ ህመሞች
- ኤች አይ ቪ፣ ቲቢ፣ የምግብ እጥረት ፣ ኩፍኝ፣
- የቫይታሚን ኤ ማጠር ይገኙበታል እንዚህ በተለይም የተቅማጥ መደጋገም እድልን ይጨምራሉ።
- ተቅማጥ፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት ማጣት፣መጠነኛ ትኩሳት
- በሰውነት ፈሳሽ መመናመን ምክንያት፡ የከንፈር መድረቅ የአይን መጎድጎድ ውሃ ሲያዩ መንገብገብ ለመጠጣት መቸኮል ሊታይ ይችላል
- የጸና የፈሳሽ እጥረት ሲኖር ደግሞ የንቃት ማጣት ውሃ አልጠጣም ማለት ይታያል (ይህ ሲከሰት ቶሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣት እና ተገቢውን ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል)
- የሰውነት ፈሳሽ መመናመን
- የንጥረነግሮች መጠን መዛባት
- ሲደጋገም ደግሞ የእድገት መቀንጨርን ያመጣል።
- የከንፈር መድረቅ
- የአይን መጎድጎድ
- ውሃ ሲያዩ መንገብገብ ወይም ውሃ አልጠጣም ማለት የንቃት ማጣት እነዚህን ምልክቶች ሲመለከቱ ወደ ድንገተኛ ክፍል ቶሎ በመምጣት የሰውነት ፈሳሻቸው በደምስር በኩል እንዲተካ ማድረግ ያስፈልጋል።
- ከላይ ያሉት ምልክቶች ከሌሉ ግን ተቅማጥ በተፈጠረ ቁጥር የሚተካ ለምለም (ኦአረኤስ) በ1ሊትር ውሃ በመበጥበጥ በት ውስጥ በየአንድ ተቅማጥ ከ2ዓመት በታች ላሉ ህጻናት ከ50-100ሚሊ ለምለም ከ2ዓመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ደግም ከ100-200ሚሊ ለምለም መስጠት የገባል።
- ከዚህ በተጨማሪ ዚንክ የተሰኘውን ንጥረነገር መስጠት ህጻናቱ ቶሎ እንዲያገግሙ እና ድጋሚ በተቅማጥ የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል።
በክትባት መከላከል ከምንችላቸው የተቅማጥ ምክንያቶች አንዱ ነው። ከ3ወር እስከ 3 ዓመት እድሜ ላይ ያሉ ህጻናትን የበለጠ ያጠቃል። ምልክቶቹም
- ትኩሳት፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ የሰውነት ፈሳሽ መመናመንን ተከትለው የሚከሰቱ የከንፈር መድረቅ፣ የአይን መጎድጎድ፣ውሃ ሲያዩ መንገብገብ ወይም ውሃ አልጠጣም ማለት የንቃት ማጣትን የመሰሉ ምልክቶች ይገኙበታል። ለመከላከል ክትባቱን መውሰድ ያስፈልጋል ይህም እስከ 98% የመከላከል አቅም አለው።
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.