የማህጸን እጢ የማህጸን ግድግዳ ህዋሲች ከተለመደው በተለየ በማደጋቸው ምክንያት የሚፈጠር እጢ ነው። በጣም የተለመደ እና እስከ 25% ሴቶችን የሚያጠቃ ህመም ሲሆን፣ የማህጸን ቀዶ ህክምና ከሚደረጉባቸው ህመሞች ዋነኛው ነው። በአብዛኛው ከ30-40 አመት ሴቶችን የሚያጠቃ ህመም ነው።
- እድሜ፡ ከ30-40 ያለው እድሜ ክልል
- ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት
- በቤተሰብ ውስጥ ያለ ተመሳሳይ ህመም
- የደም ግፊት በሽታ
- ያልወለደች ሴት
- ከፍተኛ ህመም ያለው የወር አበባ
- የወር አበባ መብዛት ወይንም ለረዥም ግዜ መፍሰስ
- ከእንብርት በታች ያለ ህመም
- የሆድ ድርቀት
- የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
- የደም ሴል መጠን ምርመራ፡ በተለይ በወር አበባ መብዛት የተነሳ የሚፈጠር የደም ማነስ ካለ ለማጣራት
- አልትራሳውንድ
- እንደ በሽተኛው ሁኔታ በሃኪም ከማህጸን ግድግዳ ላይ ናሙና መውሰድ ሊወሰን ይችላል።
ህክምና መጀመር ምልክት ለሚያሳዩ ታሚሞች ከበሽተኛው ሁኔታ በሃኪም ይወሰናል ካሉት የህክምና አማራጮች ውስጥ፡
- የወሊድ መከላከያ እንክብል እና ሌሎች የሚዋጡ መድሃኒቶች
- የቀዶ ህክምና ይገኙበታል።
- እርግዝና ሲኖር፡ የጽንስ መጨናገፍ ፣ የፅንስ አቀማመጥ ችግር የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት፣ ከጊዜው ቀድሞ የሚጀምር ምጥ
- መሃንነት
- በወር አበባ መብዛት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ
This information is for awareness only and does not replace a doctor's advice.