የቤተሰብ ዕቅድ መጠቀም የታሰበበትና የታቀደበት እርግዝና እንዲኖር በማድረግ የእናቶችንና የሕጻናትን ጤና ይጠብቃል።በተጨማሪም የትዳር አጋሮች የፈለጉትን ያህል ልጆች በፈለጉት የጊዜ ልዩነት እንዲወልዱ በማስቻል የቤተሰቡን እንዲሁም የሃገሩ ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ጫና ያደርጋል። ከስነተዋልዶ ጤና ጋር ታያይዘው ከሚጠቀሱ መብቶች መካከል አንዱ ነው።
እነዚህ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች በሀገራችን በስፋት ከምንጠቀማቸው መካከል ናቸው። በዋነኛነት ሁለት ናቸው፡- አንደኛው 28 ፍሬዎች ያሉት ሲሆን 21 የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች እና 7 በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት የደም መፍሰስን የሚተካ አይረን የሚባል ንጥረነገር የያዙ እንክብሎች ይዟል። ሁለተኛው ደግሞ 28 ፍሬዎች ያሉት ሲሆን 28ቱም የወሊድ መቆጣጠሪያ ናቸው። ሁለቱም የእንክብል አይነቶች በየቀኑ የሚወሰዱ ናቸው።
ጥቅሞች ውጤታማ የወሊድ መቆጣጠርያ መንገድ ናቸው(98-99%)
- በወር አበባ ወቅት የሚፈሰውን ደም ይቀንሳል እንዲሁም በብዙ ደም
- መፍሰስ ምክንያት የሚመጣ የደም ማነስን ይቀንሳል
- በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመምን ይቀንሳል
- ከማህጸን እጢ በሽታዎች ይከላከላል
- የማህጸን ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይቀንሳል የጎንዮሽ ጉዳቶች
- ማቅለሽለሽና ማስታወክ
- የጡት ህመም
- ክብደት መጨመር
- ፊት ላይ የሚወጣ ማድያት
- የራስ ምታት
- የደም መርጋት እድል መጨመር
ሶስት የተፈጥሮአዊ ወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች አሉ እነሱም፡
- ለተወሰነ ጊዜ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በመቆጠብ የሚተገበር የመከላከያ አይነት ነው ይህ ዘዴ የሚፈጸመው በወር አበባ ጊዜ ከ 11-17 ባሉት ቀናት ከግብረስጋ ግንኙነት በመቆጠብ ነው።
- በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር ከብልቱ ከመውጣቱ በፊት ግንኙነትን በማቋረጥ የሚተገበር የወሊድ መቆጣጠሪያ አይነት ነው::
- ጡት ማጥባት - ጡት የሚያጠቡ እናቶች በተለይ በመጀምሪያዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ የወር አበባ አያዩም
(የማርገዝ እድላቸውም በጣም ዝቅተኛ ነው)
ይህ ዘዴ ውጤታማ የመሆን እድል ያለው ፡ በመጀመሪያ 6ወራት ውስጥ፣ በየ2-3 ሰዓት
ልዩነት በደንብ ማጥባት ሲኖር እና እናቲቱ የወር አበባ እያየች ካልሆነ ነው።
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ የሚከናወነው በቀላል ቀዶ ጥገና በባለሞያ አማካኝነት ነው። የሚያገለግለውም በቀሪ የህይወት ዘመናቸው ልጅ መውለድ ለማይፈልጉ ጥንዶች ነው። ጥቅሞች
- ከፍተኛ ውጤታማነት አለው
- ለቀሪ ህይወት ሙሉ የሚቆይ የመከላከል ጥቅም አለው የጎንዮሽ ጉዳቶች
- ተመልሶ የማርገዝ እድል በጣም አናሳ ነው
- የቀዶ ህክምና ጋር ተያይዞ የሚመጣ ጎንዮሽ ጉዳት ተጠቂ ያረጋል
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ በየ 3 ወሩ የሚሰጥ ሲሆን ከፍተኛ(99.5% ውጤታማነት) የመከላከል አቅም ያለው ነው ።
ጥቅሞች
- ከፍተኛ ውጤታማነት አለው
- የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት አያመጣም
የጎንዮሽ ጉዳቶች
- ክብደት መጨመር
- የወር አበባ መዛባት
- የአጥንት መሳሳት ተጋላጭነትን ይጨምራል
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ በክንድ የሚቀበርና ከ3-5 ዓመት(እንደ አይነቱ የሚለያይ ጊዜ) የሚያገለግል ነው ፤ ውጤታማነቱም 99% ነው። ጥቅሞች ● ልጅ መውለድ በሚፈልጉበት ጊዜ በቀላሉ አስወጥቶ ማርገዝ ይቻላል።
የጎንዮሽ ጉጉዳቶች
● ክብደት መጨመር ● የወር አበባ ኡደት መዛባት ● የክርን ህመም
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ በባለሞያ አማካኝነት በማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን ከ 8-10 ዓመት እርግዝናን ይከላከላል ሁለት አይነቶች አሉ፤ አንደኛው ሆርሞን በውስጡ የያዘው ሚሬና የሚባል ሲሆን ሌላኛው ደሞ ምንም አይነት ሆርሞን የሌለው ኮፐር አዩዲ ነው። ኮፐር አዩዲ በተለይ የሆርሞን ጎንዮሽ ጉዳትን ለማይፈልጉ ሴቶች የሚመከር አማራጭ ነው።
ጥቅሞች
- ርካሽ ነው
- ለረጅም ጊዜ ወሊድን ይከላከላል
- ለድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠሪያ ያገለግላል
ጎንዮሽ ጉዳቶች
- የማህጸን ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይጨምራል
- የወር አበባ ኡደት መዛባት
- በወር አበባ ጊዜ ህመም ያስከትላል
- የጀርባ ህመም
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ጥንቃቄ ያልተሞላው የግብረስጋ ግንኙነት ከተደረገ ወይም በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም ከተቀደደ በኋላ እርግዝናን ለመከላከል የሚጠቅም ነው። የግብረ ስጋ ግንኙነት በተደረገ የመጀመሪያ 72 ሰዓታት(እስከ 5 ቀን የሚሰራ አማራጭ አለ) ውስጥ መወሰድ ያለበት ሲሆን፣ እንክብሉን የሚንወስድበት ጊዜ ከግብረስጋ ግንኙነት ሰዓት በራቀ ቁጥር የእርግዝና መከላከል አቅሙ እየቀነሰ ይሄዳል።
ጥቅሞቹ
- ድንገተኛ የሆነ እርግዝናን ይከላከላል
- ርካሽ ነው
- በቀላሉ መጠቀም ይቻላል
ጎንዮሽ ጉዳቶች
- ለአጭር ጊዜ ነው የሚያገለግለው
- በተደጋጋሚ መወሰድ የለበትም (በድንገተኛ ጊዜ ብቻ ነው መጠቀም ያለቦት!)
ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ብዙዎች የሚጠቀሙት እና ተደራሽነት ያለው ሲሆን ለአጠቃቀም ቀላል ነው የወንዶች ኮንዶም እርግዝናን የመከላከል አቅሙ ከ88%-98% ሲሆን የሴቶች ኮንዶም ደግሞ ከ79%-95% ነው
- ጥቅሞች
- ርካሽ ፣ ተደራሽና ለአጠቃቀም ቀላል ነው
- የሰውነት ሆርሞን ላይ ለውጥ አያመጣም
- በግብረስጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ይከላከላል
- የጎንዮሽ ጉዳቶች
- የአጠቃቀም ችግር ካለ የመከላከል ጥቅም አይኖረውም
- የኮንዶም መቀደድ ሊከሰት ይችላል
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።