የእንቅርት በሽታ የታይሮይድ መጠን መጨመር ወይም መቀነስ ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን አንገት ላይ ያለ እብጠትን በመፍጠር ይታወቃል በእኛ ሃገር ከአዮዲን ማነስ ጋር በመያያዝ የሚፈጠር የእንቅርት በሽታ የተለመደ ሲሆን፤ በተለይም የሰሜን ኢትዪጵያ አካባቢ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። ታይሮይድ የሚባለው ሆርሞን ማንስ ወይም መብዛት ከእንቅርት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፡ የታይሮይድ ማነስም ሆነ መብዛት በራሳቸው የተለያዩ ምልክቶችን ያስከትላሉ።
የአዮዲን ማነስ ከእንቅርት ጋር ከሚገናኙ ምክንያቶች ዋነኛው ነው እንደ ጥቅል ጎመን ያሉ ምግቦች የአዮዲን መጠንን በመቀነስ ይታወቃሉ። ይህንንም አዮዲን ያለው ጨው በመመገብ መቅረፍ ይቻላል። የአዮዲን ማነስ በታይሮይድ ማነስ የሚመጣ እንቅርትን የሚያስከስት አጋላጭ ሁኔታ ነው የታይሮይድ መብዛትን ተከትሎ ለሚመጣ እንቅርት አጋላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ደሞ በቤተሰብ ወይም በዘር መጋለጥ ነው። ከአዮዲን ጋር ማይገናኝ እንቅርት በብዛት መከላከያ መንገድ የለውም ስለሆነም በሽታው ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ወደ ህክምና ማእከል በመሄድ እና በመታከም ብቻ መስተካከል የሚችል ነው።
እብጠቱ በሚያመጣው ጫና የሚፈጠሩ ምልክቶች
- መዋጥ መቸገር
- ትንፋሽ ማጠር
- ድምጽ መለወጥ
- ፊት ማበጥ ታይሮይድ ማነስ ሲኖር የሚኖሩ ምልክቶች
- የምግብ ፍላጎት ማጣት
- ውፍረት
- እንቅልፍ መብዛት
- ትኩረት ማጣት
- ድካም
- ሆድ ድርቀት
- ብርድ ብርድ ማለት ታይሮይድ ሲበዛ ሚኖሩ ምልክቶች
- ከተለመደው የበለጠ ረሃብ
- የሰውነት መወፈር
- እንቅልፍ ማጣት
- ብስጩ መሆን
- መወበቅ ወይም ሙቀት ሙቀት ማለት
- ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት
- ድካም
- የታይሮይድ መብዛት ሲኖር የሚታዘዙ መድሃኒቶች
- Propylthiouracil(PTU)፡ የሆርሞኑን መጠን ለመቀነስ ያገለግላል
- Carbimazole፡ የሆርሞኑን መጠን ለመቀነስ ያገለግላል
- Propranolol፡ የልብ ምትን ለማስተካከል
- የታይሮይድ ማነስ ሲኖር የሚታዘዙ መድሃኒቶች
- Levothyroxine፡ ታይሮይድን የሚተካ መድሃኒት ነው
- እንዲሁም በሃኪም ውሳኔ የቀዶ ህክምና ሊደረግ ይችላል።
- ታይሮይድ መጠን ማጣሪያ መገዶች- TSH,T3,T4 እነዚህ የሆርሞኑን ማነስ ወይም መጨመር ለማጣራት የሚረዱ ናቸው
- የአንገት አልትራሳውን- የእብጠቱ መንሰኤ እንቅርት መሆኑን ለማጣራት ይረዳል
- በመርፌ የሚወሰድ ናሙና(FNAC)- እንቅርቱ አጠራጣሪ ሲሆን እንደ ካንሰር ያሉ አሳሳቢ ህመሞችን መኖራቸውን ለማጣራት የሚደረግ ምርመራ ነው
- ኢሲጂ - በሆርሞኑ መብዛት የተነሳ ልብ ላይ የተፈጠረ ጫና መኖሩን ለማጣራት የሚደረግ ምርመራ ነው
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።