ዳማከሴDamakese

የህጻናት አመጋገብ

ጡት ብቻ መጥባት አለባቸው የተፈጥሮ አስገራሚ ስጦታዎች መካከል የጡት ወተት እንዱ ነው። ሁሉም እናት ልጆቹን በመጀመሪያ 6 ወራት ውስጥ ጡት ብቻ ማጥባት አለበት በአጠቃላይ ደግሞ ለህጻኑ የመጀመሪያ 2 ዓመታት ከሌሎች ምግቦች ተጨማሪ ጡት ማጥባት መቀጠል አለበት። በመጀመሪያ 6 ወራት ውስጥ አንድ እናት በየ2ሰአት ልዩነት በዓማካኝ በቀን 8 ጊዜ ልጇን ጡት ማጥባት አለባት። ጡት ማጥባት ለመጀመሪያ ጊዜ እናቶች ግራ ሊገባ ይችላል። ትክክለኛ የማጥባት መንገድን ማወቅ ህጻናት ከጡት የሚገኘውን ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ይረዳል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።