የአይን ሞራ የአይን ብሌን በበተለያዩ ህዋሳት ሲሸፈን የሚፈጠር ህመም ነው። ያጋጠማቸው ሰዎች እንደሚገልጹት ከሆነ በጉም በተሸፈነ መስታወት እንደማየት ያለ ስሜት የሚፈጠር ሲሆን፤ ቀስ በቀስ እይንታን ከሚጋርዱ የአይን ህመሞች አንዱ ነው። ቀስ ብሎ በመፈጠሩ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ከዘገየ በኋላ ነው የሚለዩት።
- የእይታ ብዥ ማለት፣ መጋረድ
- በተለይ ማታ ላይ የማየት አቅም መቀነስ
- ብርሃናማ ክብ ክብ ነገሮች መመልከት
- ለማንበብ መቸገር ወይንም ከፍተኛ ብርሃን መፈለግ
- አንድ ነገር ሁለት መስሎ መታየት
የአይን ሞራ በአብዛኛው ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ ብሌን ውስጥ የሚገኙ ፕሮቲኖች ሲሰባበሩ እና ንጻቱን ሲቀንሱት የሚፈጠር ህመም ቢሆንም እንኳን፤ ለዚህ ሚያጋልጡ ነገሮች አሉ
- አይን ላይ የደረሰ አደጋ
- የስኳር በሽታ
- እንደ ስቴሮይድ ያሉ መድሃኒቶች
- ማጨስ
- ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት
- የጸሃይ ብርሃን መብዛት
- ከዚህ በፊት የተደረገ የአይን ቀዶ ህክምና
- ከማጨስ መቆጠብ
- የስኳር በሽተኛ ከሆኑ ጥሩ የሆነ የበሽታው ቁጥጥር መኖር
- በየጊዜው የአይን ህክምና በማድረግ
- የጸሃይ መከላከያ መነጽር መጠቀም
የአይን ቀዶ ህክምና
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።