ዳማከሴDamakese

የአንጀት መቆጣት

የአንጀት መቆጣት ከቃሉ እንደምንረዳው የአንጀት ግድግዳ ላይ በየግዜው የሚነሳ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ቁስለት እና መቆጣት ሲኖር የሚፈጠር ህመም ነው። ሁለት አይነት የአንጀት መቆጣት ህመሞች አሉ እነሱም

  1. አልሰሬቲቭ ኮላይተስ እ
  2. ሮንስ ዲዚዝ በመባል ይታወቃሉ። የተለያዩ የአንጀት አካላትን ቢያጠቁም እንኳን በምልክት እና ህክምና ተቀራራቢ የሆኑ ናቸው። የአንጀት መቁሰልን የሚፈጥረው ይህ ነው ብሎ መለየት ባይቻልም የተለያዩ የሚገመቱ መንገዶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ በሊስቴኢያ፣ ሚዝልስ፣ ፓራ ቲበርኩሎሲስ መያዝ የሚጠረጠር መንገድ ነው። የአንጀት መቆጣት በአብዛኛው ከ 20-40 ባለው እድሜ ክልል ውስጥ የሚታይ ህመም ሲሆን በተለይም ሴቶች ላይ የበለጠ ይከሰታል። በዘር ግንድ ከጥቁሮች ይልቅ ነጮች ላይ የበለጠ የሚታይ ህመም ነው።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።