የማጅራት ገትር በሽታ አንጎል እና አንጎልን ሸፍኖ የሚገኘው ክርታስ በኢንፌክሽን በሚጠቁበት ጊዜ የሚፈጠር ህመም ነው። በጊዜ ካልታከመ የሚጥል በሽታ፣ የሰውነት መስነፍ፣ የጆሮ እና አይን ስራ ማቆም፣ የአእምሮ አቅም መቀነስ፣ እና እስከ ሞት የሚያደርሱ አስከፊ ውጤቶችን የሚያደርስ አስፈሪ በሽታ ነው። እንደ ሌሎች ኢንፈክሽኖች ሁሉ አዳጊ ሃገር በመሆናችን ከፍተኛ ተጋላጭነት በሃገራችን ይታያል። ይህ ህመም በባክቴሪያ፣ ቫይረስ ፣ ፈንገስ እና ቲቢ ሊከሰት ይችላል፣ መንሰኤውን መለየት ተገቢውን መድሃኒት በመስጠት ህመሙን ቶሎ ለማዳን ይረዳል።
- እድሜ ከ1 ወር በታች ወይም ከ 50 ዓመት በላይ መሆን
- ክትባት ያለመከተብ
- እንደ ኤች አይ ቪ ያሉ የበሽታ መከላከልን የሚቀንሱ ተጓዳኝ ህመሞች
- አልኮል ማብዛት
- የሚጥል በሽታ
- ጭንቅላት መመታት እና የራስ ቅል ስብራት
- አንጎል ላይ የሚደረግ የቀዶ ህክምና
- ትኩሳት
- ራስ ምታት
- የአንገት መጨምደድ
- የንቃት መጠን መቀነስ
- ብርሃን መሸሽ
- ማቅለሽለሽ
- የሰውነት አካል መስነፍ
- የእይታ ለውጥ(ነገሮች ሁለት ሆነው መታየት) ወዘተ ከላይ የተጠቀሱት ከመፈጠራቸው በፊት በብዛት ጉንፋን የመሰለ ምልክት በታማሚዎች ላይ ይታያል ይህም የሚሆነው አብዛኛውን ጊዜ ከአየር ቧንቧ ኢንፈክሽን ተነስቶ ወደ አንጎል የሚንሰራፋ ባክቴሪያ የሚፈጥረው የማጅራት ገትር በሽታ ላይ ነው።
- አጋላጭ ሆኔታዎችን ማስተካከል የተጋላጭነት እድልን ይቀንሳል
- ልጆችን ክትባት ማስከተብ ደሞ አብዛኛውን(በኒሞኮከስ የሚፈጠር) የማጅራት ገትር በሽታ በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ እድል አለው።
- የደም ሴል መጠንን የሚያጣራ ምርመራ
- ከጀርባ የሚቀዳ የህብለሰረሰር ውሃን በላቦራቶሪ በመመርመር መንሰኤውን እና የበሽታውን መኖር ማጣራት።
- ሲቲ ስካን ወይም ኤም አር አይን የመሳሰሉ ምርመራዎች እንደአስፈላጊነቱ በሃኪም ውሳኔ ሊታዘዙ ይችላሉ።
- ብዙውን ጊዜ በደም ስር የሚሰጡት አንቲባዩቶኮች ይሰጣሉ
- እንደታካሚው ሁኔታ እና የአስከፊ ውጤቶች መከሰት ተጨማሪ ህክምና በድንገተኛ ክፍል ውስጥ ይሰጣል።
ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።