ዳማከሴDamakese

ስኪዞፍሬንያ

ስኪዞፍሬንያ(በተለምዶ እብደት የምንለው ህመም) በአካል እና በአእምሮ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለው የአእምሮ ህመም ነው። እንደ ሃሳብ፣ ትውስታ፣ ስሜት እና ባህሪ ባሉ ነገሮች ላይ ጣልቃ በመግባት አንጎል በትክክል እንዳይሰራ ይረብሸዋል። በዚህም ምክንያት በዕለት ተዕለት የማህበራዊ እና የስራ ሕይወት ላይ ጉዳት ያደርሳል። ያልታከመ ስኪዞፈሪንያ ብዙውን ጊዜ ግንኙነቶችን(ሙያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ የፍቅር እና ሌላ) ያበላሻል። ስኪዞፍሬንያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 221 ሰዎችን ይጎዳል። ብዙውን ጊዜ በወንዶች ላይ ከ15-25 ባለው እድሜ እንዲሁም በሴቶች ላይ ደሞ ከ25-35 ባለው የእድሜ ክልል ላይ የሚጀምር ህመም ነው። ስኪዞፍሬንያ የእድሜ ልክ በሽታ ነው ሙሉ በሙሉ ከህመሙ የሚፈውስ መድሃኒት የለም ታማሚዎችም በተለያዩ ጊዜያት ህመሙ ሊያገረሽባቸው እና ሆስፒታል ተኝተው መታከም ሊጠበቅባቸው ይችላል። ነገር ግን ያሉትን የህክምና አማራጮች በትክክል በመከተል እንደ ማንኛውም ሰው ሙያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን በመተግበር ጠቃሚ ዜጋ መሆን ይቻላል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።