ዳማከሴDamakese

ጭርት

በፈንገስ የሚፈጠር እና ሰውነት ላይ ሽፍታን የሚያመጣ በሽታ ነው። የማሳከክ ስሜት የሚያመጣ እና ክብ የሆነ ሽፍታ ሲሆን ከተለመዱት የቆዳ ህመሞች አንዱ ነው። ከሰውነት ቆዳ ተጨማሪ በእግር ላይ(በተለምዶ የአትሌት እግር የተሰኘው)፣ በጭንቅላት ላይ ሊወጣ ይችላል። በነዚህ የተለያዩ አካላት ላይ ሲከሰት የፈንገሶቹ ዝርዮች ይለያያሉ። በቆዳ ንክኪ ከሰው ወደ ሰው እና ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል።

ይህ መረጃ ለግንዛቤ ብቻ ነው፤ የሐኪም ምክርን አይተካም።